ብቸኝነት ፡ አይስማኝም (Bechegninet ayisemagnim) (1) - ይድነቃቸው ተካ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይድነቃቸው ተካ
(Yidnekachew Teka)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ
(Eyesus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ ((2005))
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 7:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

ብቸኝነት አይሰማኝም
ብቻዬን አይደለሁም
ኧረ አለ መፅናኛዬ አለ
ኧረ አለ መበርቻዬ አለ
ኧረ አለ መነሻዬ አለ
ኧረ አለ ቤቴን ሞልቶት አለ
       ብቸኝነት አይሰማኝም
       ብቻዬን አይደለሁም
        ኧረ አለ መፅናኛዬ አለ
        ኧረ አለ ሳያስነካኝ አለ
        ኧረ አለ ደባቂዬ አለ
        ኧረ አለ መነሻዬ አለ
መፅናኛዬ አለ ኦሆ
መበርቻዬ አለ
የኔ ሞገስ አለ ሆሆ
ልቤን ሞልቶት አለ
የሩቅ ዘመን ክብሬ አሄ
መነሻዬ አለ
የኔ ሞገስ አለ ሆሆ
መበርቻዬ አለ

አንዴ ነክተኸኛል ሌላውን ለምጄ መኖር አልችልም
ተሸንፊያለሁ ኢየሱስ በፍቅርህ መቼም ያንተ ነኝ
አንዴ ነክተኸኛል ሌላውን ለምጄ መኖር አቃተኝ
ተሸንፊያለሁኝ ኢየሱስ በፍቅርህ መቼም ያንተ ነኝ

    ፍቅርህ ልቤ ውስጥ አለ
    ፍቅርህ አጥንቴ ውስጥ
    ፍቅርህ መንፈሴን ዘልቋል
    ፍቅርህ አጥለቅልቆኝ

ኧረ ፍቅርህ ልቤ ውስጥ እለ
ፍቅርህ አጥንቴ ውስጥ አለ
ፍቅርህ መንፈሴን ሞልቷል

ፍቅርህ አጥለቅልቆኝ
ለሌላው መኖር አልችልም ገብተሀል መላ እኔነቴ
ለሌላው መሆን አልችልም ያንተ ነኝ ኢየሱስ አባቴ
ለሌላው መሮጥ አልችልም ያንተ ነኝ ኢየሱስ አባቴ
ለሌላው መኖር አቃተኝ ነክተኸኛል ኢየሱስ አባቴ

  ክብር ዝናን ቶሎ እለምዳለሁ
  ብሩ ወርቁን ቶሎ እለምዳለሁ
  ሲያወሩኝ እሰለቻለሁ
  ሲነግሩኝ ልቤን አይሞቀው
 
ቀን ከሌት የማልጠግብህ
ቢያወሩኝ የማልሰለችህ
ገብተሀል መላ እኔነቴ
ወደድኩህ ኢየሱስ አባቴ
ወደድኩህ ኢየሱስ አባቴ
        
        ብቸኝነት አይሰማኝም ብቻዬን አይደለሁም
        ኧረ አለ መፅናኛዬ አለ
        ኧረ አለ ሳያስነካኝ አለ
        ኧረ አለ ደባቂዬ አለ
        ኧረ አለ መነሻዬ አለ

መፅናኛዬ አለ ኦሆ
መበርቻዬ አለ
የኔ ሞገስ አለ ሆሆ
ልቤን ሞልቶት አለ
የሩቅ ዘመን ክብሬ አሄ
መነሻዬ አለ
የኔ ሞገስ አለ ሆሆ
መበርቻዬ አለ

     የእርሱን ጓደኝነት የምተካበት
          ጎደኛ የለኝም
     የእርሱን ወዳጅነት የምተካበት ወዳጅ የለኝም
          እኔ አላየሁም *2
    እኔ አላየሁም እንደ ኢየሱስ እኔ አላየሁም
          እኔ አላየሁም *2
         ኧረ እንደ እየሱስ አልገጠመኝም

    ክብር ዝናን ቶሎ እለምዳለሁ
    ብሩ ወርቁን ቶሎ እለምዳለሁ
    ሲያወሩኝ እሰለቻለሁ
    ሲነግሩኝ ልቤን አይሞቀው
 
ቀን ከሌት የማልጠግብህ
ቢያወሩኝ የማልሰለችህ
ገብተሀል መላ እኔነቴ
ወደድኩህ ኢየሱስ አባቴ
ወደድኩህ ኢየሱስ አባቴ

      አውሩልኝ ስለ ኢየሱስ
       ንገሩኝ ስለ ኢየሱስ
       ዘምሩልኝ ስለ ኢየሱስ
       እርሱ ነው የህይወቴ ሱስ