ቸኮለብኝ ፡ ልቤ (chekolebegn Lebie) - ይድነቃቸው ፡ ተካ አበቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ አበቱ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegneh)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ አበቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

ሌላ ነገር ታገስ ብትለኝ
ጠብቃለሁ እስኪሆንልኝ
ግን አባቴ ለክብርህ ነገር
በህልውናህ ውሎ ለማደር

ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ
ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ
አንተን ማየት ክብሬ ጉጉቴ (፪)

ኢየሱስ አይኔ በርቶ አንዴ ልይህ
ኢየሱስ ውስጤ ራበህ እስከምነካህ
ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ
ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (፪)

ቸኮለብኝ ልቤ ሊያገኝህ
እንዴት ብዬ ኢየሱስ ልያዝህ
ናፍቆቴ ነህ የሁሌ አምሮቴ
(አንተን ማየት ክብሬ ጉጉቴ) (፪)
አባትዬ ፊትህ ጉጉቴ
ኢየሱስዬ ክብርህ ጉጉቴ
አባትዬ ክብርህ ጉጉቴ

ኢየሱስን የነካው ሰው
ኢየሱስን ባይኑ ያየ ሰው
ኢየሱስ የገባው ሰው
ኢየሱስን ባይኑ ያየ ሰው
(ለሌላ ነገር መኖር አይችልም) (፪)
(ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም) (፪)

የመቅደስን ደጅ የሚጠኑ
ብዙ ናቸው አንተን የሚሹ
አምላክህን አሳየኝ የሚሉኝ
ክብሩ የታል እስቲ አሳውቀኝ

ወዴት ልበል የት ጋር ነህ ውዴ
በኔ ዘመን ይረፍ ትውልዴ
ከኔ ውጪ የትም አጠቁም
በኔ ላይ እስኪያይህ ሁሉም (፪)

ኢየሱስ አይኔ በርቶ አንዴ ልይህ
ኢየሱስ ውስጤ ራበህ እስከምነካህ
ኢየሱስ እኔ አልችልም መኖር ካለዚያ
ኢየሱስ በሌለበት ክብርህ ህልውናህ (፪)

የጭንቅ ነው ስጠራህ ውዴ
የውስጤን ምጥ ቃላት ሰብስቤ
ቢነግርልኝ የልቤን ጩኸት
የጥማቴን የረሃቤን ልክ

እስከመቼ እንዲሁ በልማድ
ያሰለቻል ሲደገም ትላንት
በሱ ክብር በሱ ህልውና
አዲስነት በየማለዳ (፪)

ኢየሱስን የነካው ሰው
ኢየሱስን ባይኑ ያየ ሰው
ኢየሱስ የገባው ሰው
ኢየሱስን ባይኑ ያየ ሰው
(ለሌላ ነገር መኖር አይችልም) (፪)
(ለፈለገው ነገር መኖር አይችልም) (፪)