የመልካምነትህ (Yemelkameneteh) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

ሁልጊዜ ፡ እኔ ፡ የሚገርመኝ
ራሴን ፡ ሳየው ፡ ስቃኘው ፡ ኋላዬን
በሄድኩበት ፡ በሕይወት ፡ መንገድ
ያሳረፍከኝ ፡ አለ ፡ ምልክት
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የመልካምነትህ

አዝ:- አቤት ፡ የመልካምነትህ
አቤት ፡ የአባትነትህ
አቤት ፡ እኔን ፡ አኑረሃል
አቤት ፡ እንዲህ ፡ አሳድገህ (፪x)
ዓይኖቹን ፡ አንስቶ ፡ አንተን ፡ የጠበቀ (፫x)
መች ፡ እንዲሁ ፡ ይቀራል ፡ ትጐበኘዋለህ (፫x)
ተሰብረህ ፡ ማትወጋ ፡ ለተደገፉብህ (፫x)
አቅም ፡ ትሆናለህ ፡ በእውነት ፡ ለሚጠሩህ (፫x)

ስለአንተ ፡ ላወራ ፡ እኔም ፡ ልናገር
እድሉን ፡ አገኘሁ ፡ ከአረክላቸው ፡ ጋር
በአንተ ፡ ነው ፡ ያየሁት ፡ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ለራሴ
ወደ ፡ ደካማው ፡ ሰው ፡ ስትመጣ ፡ ኢየሱሴ (፪x)

እንዴት ፡ ነው ፡ ምትወደኝ ፡ እኔን
ምንም ፡ ሳልሰራልህ ፡ ለምን
ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያለህ
እኔን ፡ የወደድክበት (፪x)

እኔማ (፰x) ፡ እኔማ ፡ ያየሁት ፡ ኢሄን ፡ ነው
እኔማ ፡ ኢየሱስ ፡ በዘመኔ
እኔማ ፡ መልኩን ፡ ልጥራው
እኔማ ፡ ባወራው ፡ ከልቤ

አዝ:- አቤት ፡ የመልካምነትህ
አቤት ፡ የአባትነትህ
አቤት ፡ እኔን ፡ አኑረሃል
አቤት ፡ እንዲህ ፡ አሳድገህ (፪x)
ዓይኖቹን ፡ አንስቶ ፡ አንተን ፡ የጠበቀ (፫x)
መች ፡ እንዲሁ ፡ ይቀራል ፡ ትጐበኘዋለህ (፫x)
ተሰብረህ ፡ ማትወጋ ፡ ለተደገፉብህ (፫x)
አቅም ፡ ትሆናለህ ፡ በእውነት ፡ ለሚጠሩህ (፫x)

ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታ ፡ አጠገብከኝና
ዘመኔ ፡ ለምልሟል ፡ ብርሃንህ ፡ በራና
ሕይወቴን ፡ የገዛ ፡ የድንግዝግዝ ፡ ኑሮ
ላላየው ፡ አለፈ ፡ ሁሉ ፡ ተቀይሮ (፪x)

እንዴት ፡ ነው ፡ ምትወደኝ ፡ እኔን
ምንም ፡ ሳልሰራልህ ፡ ለምን
ምን ፡ ዐይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያለህ
እኔን ፡ የወደድክበት (፪x)

እኔማ (፰x) ፡ እኔማ ፡ ያየሁት ፡ ኢሄን ፡ ነው
እኔማ ፡ ኢየሱስ ፡ በዘመኔ
እኔማ ፡ መልኩን ፡ ልጥራው
እኔማ ፡ ባወራው ፡ ከልቤ