የሕይወቴ ፡ ክብር (Yehiwotie Keber) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
የሕይወቴ ፡ ክብር ፡ የመኖሬ ፡ ግብ ፡ ነህ
ስራመድ ፡ ስቀመጥ ፡ ሁልጊዜ ፡ ማልምህ
ኢየሱሴ ፡ እስኪ ፡ ልንገርህ ፡ የልቤን ፡ ካላሳይህ
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ የቱ ፡ ክብሬ ፡ ነው
ሕይወቴን ፡ ልቤን ፡ ሚገዛው
(፪x)

አዝ:- ኧረ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ተባረከ ፡ ቢባል (፪x)
ምትቆጠርልኝ ፡ በረከቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፬x)
ኧረ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ አደገ ፡ እንኳን ፡ ቢባል (፪x)
ምትቆጠርልኝ ፡ እድገቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፬x)

በሩቅ ፡ ያሉ ፡ ሁሉ ፡ ስለእኔ ፡ ቢያወሩ
ቅርቤም ፡ ያሉ ፡ ሁሉ ፡ ስለእኔ ፡ ቢያወሩ
አቤት ፡ ተወራ/ተነገር ፡ ኢየሱስዬ
ሰው ፡ የሆንኩብህ ፡ ነህ ፡ ቁም ፡ ነገሬ
(፪x)
ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ፡ ስለእራሴ
አንተ ፡ ግን ፡ ተወራ ፡ ኢየሱሴ
ብቻህን ፡ ድንቅ ፡ ታርግ ፡ አንተ ፡ በእኔ

አዝ:- ኧረ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ተባረከ ፡ ቢባል (፪x)
ምትቆጠርልኝ ፡ በረከቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፬x)
ኧረ ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ አደገ ፡ እንኳን ፡ ቢባል (፪x)
ምትቆጠርልኝ ፡ እድገቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፬x)