ማዳኑ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው (Madanu Kef Yale New) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
ይወርሰኛል ፡ ብዬ ፡ የፈራሁት ፡ ነገር ፡ የቆመ ፡ በበር
አይሆንም ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ከሰማያት ፡ ቃል ፡ ወጣ ፡ ስለእኔ
ራራልኝ ፡ ውዴ (፪x)

ወጀብ ፡ አለ ፡ ከፊት ፡ አትፍራ ፡ አለኝ ፡ ጌታዬ
ተገልብጧል ፡ ነገሩ ፡ ቃል ፡ ወጥቷል ፡ ዛሬ ፡ ለእኔ
በመንገድ ፡ ሊያስቀረኝ ፡ ሊገታኝ ፡ የነበረ
ቀደምኩት ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ ወጥመዱ ፡ ተሰበረ

ማነው ፡ ማዕበሉን ፡ የገሰጸው
ማነው ፡ ወጀቡን ፡ ጸጥ ፡ ያደረገው
ማነው ፡ ይሁን ፡ ሲል ፡ ሚሆንለት
ማነው ፡ የአፉ ፡ ቃል ፡ ሚጸናለት
ጌታዬን ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያየሁት ፡ በዘመኔ (፪x)

ፈርቶት ፡ የሩቅ ፡ ዘመኔን ፡ ቢነሳ ፡ ያ ፡ ጠላቴ
ጉልበቴን ፡ ሊያደክመው ፡ ቢቆምም ፡ በመንገዴ
ይሄዳል ፡ የኔ ፡ ነገር ፡ በቃል ፡ ሚኖር ፡ አይቆምም
ሰባሪው ፡ ከፊት ፡ ወጥቷል ፡ ሰብሬ ፡ አልፋለሁ ፡ እኔ

ማነው ፡ መንገዴን ፡ ያስጀመረኝ
ማነው ፡ መንገዴን ፡ ሚያስጨርሰኝ
ማነው ፡ ከፊቴ ፡ የቀደመው
ማነው ፡ መንገዴን ፡ የከፈተው
ጌታዬን ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ያየሁት ፡ በዘመኔ (፪x)

ንጉሥ ፡ ወርዶ ፡ ከሰማይ ፡ አይቆምም ፡ ፊቱ ፡ ከልካይ
ይታደጋል ፡ ያድናል ፡ ደርሶ ፡ ከሞት ፡ ያወጣል
እኔም ፡ የእርሱ ፡ ልጅ ፡ ሆኜ ፡ ድኛለሁ ፡ ከጠላቴ
ጠላት ፡ ያሴረው ፡ ሴራ ፡ መና ፡ ሆነ ፡ ፉከራ

ማዳኑ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው
ሲረዳኝ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው
ሲያወጣኝ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው
ጌታ ፡ ሲረዳኝ ፡ ጌታ ፡ ሲያወጣኝ