ከፊት ፡ ሁን ፡ ኢየሱሴ (Kefit Hun Eyesusie) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
ናና ፡ ከፊት ፡ ሁን ፡ ኢየሱሴ
ክብሬ ፡ ነህ ፡ አትሆንም ፡ ከኋላዬ (፬x)
በሰው ፡ መሃል ፡ ድፍረቴ
በሰው ፡ መሃል ፡ ድምቀቴ
በሰው ፡ መሃል ፡ ሕይወቴ
በሰው ፡ መሃል ፡ ውበቴ (፪x)

በማይጠቅም ፡ በማይረባ ፡ ነገር
ልለውጠው ፡ አልችልም ፡ የዘለዓለም ፡ ክብሬን
እርሱ ፡ ነው ፡ ከመሬት ፡ አንስቶ
ያሳመረው ፡ ሕይወቴን ፡ ሞገሱን ፡ አፍሶ
ዛሬ ፡ ላየኝ ፡ ሰው ፡ ጌታ ፡ እንደዚህ ፡ ሰርቶ
ማለት ፡ አልችልም ፡ እጄ ፡ አደረገችው
እኔ ፡ አሳያለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ብዬ
አልደብቀውም ፡ ክብሬን ፡ ከኋላዬ

በእርሱ ፡ እኮ ፡ ነው (በጌታ) ፣ ክብር ፡ ያየሁት (በጌታ)
ያንን ፡ ዘመን (በጌታ) ፣ የረሳሁት (በጌታ)
ሌላውን (በጌታ) ፣ ተቀየረ (በጌታ)
ክብሬ ፡ ገብቶ (በጌታ) ፣ ቤቴ ፡ አማረ (በጌታ)

ለክብሬ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ዝማሬ (አለኝ ፡ ዛሬ)
ምሥጋና (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ለጌታ (አለኝ ፡ ዛሬ)
ኢሄው ፡ እልልታ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ኢሄው ፡ ምሥጋና (አለኝ ፡ ዛሬ)
ኢሄው ፡ ሙገሳ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ኢሄው ፡ ለጌታ (አለኝ ፡ ዛሬ) (፪x)

የክብር ፡ የሞገስ ፡ አክሊሌ
ኢየሱስ ፡ ሆኖ ፡ መጣልኝ ፡ ሊለውጥ ፡ ታሪኬን
አይችልም ፡ ልቤም ፡ መራቅ ፡ ከእርሱ
እንዴት ፡ ሊሆንለት ፡ ነው ፡ ዘንግቶት ፡ ሞገሱን

ሙሽራ ፡ ጌጧን ፡ ደግሞ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጧን
ትረሳለች ፡ ወይ ፡ ውብ ፡ ያደረጋትን
እርሷ ፡ ካልረሳች ፡ እኔ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ነው
ውብ ፡ ያደረገኝን ፡ ኢየሱስን ፡ ምረሳው

በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ (በጌታ) ፣ ክብር ፡ ያየሁት (በጌታ)
ያንን ፡ ዘመን (በጌታ) ፣ የረሳሁት (በጌታ)
ሌላውን (በጌታ) ፣ ተቀየረ (በጌታ)
ክብሬ ፡ ገብቶ (በጌታ) ፣ ቤቴ ፡ አማረ (በጌታ)

ለክብሬ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ዝማሬ (አለኝ ፡ ዛሬ)
ምሥጋና (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ለጌታ (አለኝ ፡ ዛሬ)
ኢሄው ፡ እልልታ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ኢሄው ፡ ምሥጋና (አለኝ ፡ ዛሬ)
ኢሄው ፡ ሙገሳ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ኢሄው ፡ ለጌታ (አለኝ ፡ ዛሬ) (፪x)

ልቤ ፡ እምቢ ፡ ይለኛል (ሌላ) ፣ አላይ ፡ ወደ ፡ ኋላ (ሌላ)
ዓለም ፡ አትናፍቀኝ (ሌላ) ፣ ኢየሱሴን ፡ ብቻ (ሌላ) (፪x)

ለክብሬ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ዝማሬ (አለኝ ፡ ዛሬ)
ምሥጋና (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ለጌታ (አለኝ ፡ ዛሬ)
ኢሄው ፡ እልልታ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ኢሄው ፡ ምሥጋና (አለኝ ፡ ዛሬ)
ኢሄው ፡ ሙገሳ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ ኢሄው ፡ ለጌታ (አለኝ ፡ ዛሬ) (፪x)

አለኝ (አለኝ ፡ ዛሬ) ፣ እህህህ ፡ (አለኝ ፡ ዛሬ)
አለኝ ፡ (አለኝ ፡ ዛሬ) (፫x)