ክብርህ ፡ ሽልማቴ (Kebreh Shelematie) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
ሰማይና ፡ ምድርን ፡ አጸና ፡ በቃሉ
ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ ሸፈነ ፡ በክብሩ
ዐይኑን ፡ ከፍቶ ፡ ያየ ፡ እንዴት ፡ የታደለ
የእግዚአብሔርን ፡ ጥበብ ፡ ክብሩን ፡ ያስተዋለ

ሰማዩም ፡ ይናገር ፡ ምድሩም ፡ ይመስክር
የግርማ ፡ ሞገሱን ፡ የውበቱን ፡ ንገር
ሁሉን ፡ የፈጠረ ፡ ሁሉንም ፡ የሰራ
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ማነው ፡ አዬ ፡ እስቲ ፡ ይናገራ

መደርደር ፡ በገና ፡ እጄ ፡ ለምዶ
ጀመረ ፡ ሊቀኝ ፡ እጄ ፡ ለምዶ
ጌታን ፡ ወዶ ፡ አሄሄ (፪x)
መዘመር ፡ ለጌታ ፡ አፌ ፡ ለምዶ
ጀመረ ፡ ሊቀኝ ፡ አፌ ፡ ለምዶ
ጌታን ፡ ወዶ ፡ አሄሄ(፪x)
(ጌታን ፡ ወዶ) ፡ የገባዋል ፡ ብሎ
(ጌታን ፡ ወዶ) ፡ ቅኔውን ፡ ፈልጐ
(ጌታን ፡ ወዶ) ፡ ታዲያ ፡ ለማን ፡ ላዚም
(ጌታን ፡ ወዶ) ፡ ጌታዬ ፡ አለ ፡ ብሎ
(ጌታን ፡ ወዶ) ፡ አዬዬ ፣ ጌታን ፡ ወዶ ፡ አሀሀሀሀ
(ጌታን ፡ ወዶ) ፡ ወዶ ፣ (ጌታን ፡ ወዶ) ፡ ጌታን ፡ ወዶ
(ጌታን ፡ ወዶ)

ቢሆንልኝማ ፡ እህህህ ፡ ክብርህ ፡ ሽልማቴ ፡ እህህህ
ዘምሬ ፡ አልጠግበውም ፡ እኔማ ፡ እስከዘለዓለሜ
ቢሆንልኝማ ፡ እህህህ ፡ ክብርህ ፡ ሽልማቴ ፡ እህህህ
በዜማ ፡ ይሞላል ፡ የእኔ ፡ ቤት ፡ ቀንና ፡ ሌሊቴ

ይሁን ፡ ስትለው ፡ ሁሉ ፡ ሆነ
በአንደበትህ ፡ ቃል ፡ ተፈጠረ (፪x)
የሌለን ፡ ነገር ፡ ልክ ፡ እንዳለ
አንተ ፡ ስትጠራው ፡ እውን ፡ ሆነ (፪x)
ባዶ ፡ የሆነው ፡ ምድረ ፡ በዳ
ገነት ፡ ይሆናል ፡ ቃል ፡ ከወጣ (፪x)
የሞተ ፡ ነገር ፡ የቀበሩት
ጌታ ፡ ስትጠራው ፡ ይላል ፡ አቤት (፪x)

በሉት (፫x) ፡ ተባረክ ፡ በሉት
በሉት (፫x) ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ በሉት
በሉት (፫x) ፡ ጌታን ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ በሉት
በሉት (፫x) ፡ ተባረክ ፡ በሉት
በሉት ፡ ተባረክ ፡ በሉት ፣ በሉት ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ በሉት
በሉት ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ በሉት ፣ በሉት ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ በሉት

በሕይወቴ ፡ አይተው ፡ ለወደድከው ፡ ነገር
ልብህ ፡ ደስ ፡ ብሎት ፡ ስለእኔ ፡ ብትምል
ምላሽ ፡ አለኝ ፡ ብለህ ፡ ከወደድክ ፡ ልትሰጠኝ
ክብርህ ፡ ሽልማቴ ፡ አሄሄ ፡ ምነው ፡ በሆነልኝ

ቢሆንልኝማ ፡ እህህህ ፡ ክብርህ ፡ ሽልማቴ ፡ እህህህ
ዘምሬ ፡ አልጠግበውም ፡ እኔማ ፡ እስከዘለዓለሜ
ቢሆንልኝማ ፡ እህህህ ፡ ክብርህ ፡ ሽልማቴ ፡ እህህህ
በዜማ ፡ ይሞላል ፡ የእኔ ፡ ቤት ፡ ቀንና ፡ ሌሊቴ (፪x)