From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በፈረስ ፡ ውድድር ፡ ወደ ፡ ትልቁ ፡ ሜዳ
ሁሉም ፡ ተሰማርቶ ፡ በድንገት ፡ ድል ፡ ቢነሳ
ተብሎ ፡ ቢጠየቅ ፡ ማነው ፡ ያሸነፈው
ፈረስና ፡ ጌታው ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ተቀምጠው
እኔ ፡ ነኝ ፡ ሚለውን ፡ እስኪ ፡ ይጠየቅ ፡ ማነው
ጌታዪ ፡ ሆይ ፡ ድል ፡ ነህ??? ፡ ዎይ ፡ ፈረሱን ፡ እያየሁ
እንዲህ ፡ ሲል ፡ ሰማሁት ፡ እንዲህ ፡ ሲል ፡ አምላኬ
ድል ፡ አድርጌያለሁኝ ፡ እኔማ ፡ በራሴ
ስለዚህ ፡ ስንኖር ፡ በዚህች ፡ ምድር ፡ ላይ
አምላክ ፡ እንዳለው ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ተወካይ
ስለእኛ ፡ ለሞተው ፡ ደግሞ ፡ ለተነሳው
የእርሱን ፡ ክብር ፡ አንጂ ፡ የእኛን ፡ ስራ ፡ እንርሳው??
አዝ:- ክብር ፡ ይሁን ፡ ለዝናው
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ዘለዓለም
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለተገባው (፪x)
በሩጫም ፡ ውድድር ፡ ወደ ፡ ሩጫው ፡ ሜዳ
ሁሉም ፡ ተሰማርቶ ፡ በድንገት ፡ ድል ፡ ቢሰማ
ቶሎ ፡ የሚይዙት ፡ ሮጠው ፡ ይሄዱና
ባንዲራውን ፡ አይደል ፡ ሚለብሱት ፡ በተርታ
የወከላቸውን ፡ አገር ፡ መቼ ፡ ረሱ
ለስማቸው ፡ ብቻ ፡ አይሮጡም ፡ እነርሱ
እንዲህ ፡ ሲል ፡ ሰማሁት ፡ እንዲህ ፡ ሲል ፡ አምላኬ
ድል ፡ አድርጌያለሁኝ ፡ እኔማ ፡ በራሲ
ስለዚህ ፡ ስንኖር ፡ በዚህች ፡ ምድር ፡ ላይ
አምላክ ፡ እንዳለው ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ተወካይ
ስለእኛ ፡ ለሞተው ፡ ደግሞ ፡ ለተነሳው
የእርሱን ፡ ክብር ፡ አንጂ ፡ የእኛን ፡ ስራ ፡ እንርሳው???
አዝ:- ክብር ፡ ይሁን ፡ ለዝናው
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ዘለዓለም
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለተገባው (፪x)
የኔ ፡ ጌታ ፡ መሆን ፡ ያማረኝ
የኔ ፡ ኢየሱሴን ፡ ስኖር ፡ በምድር
የኔ ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ አልፈህ ፡ ሁንብኝ
የኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ??? (፪x)
ኢየሱስ ፡ ተቀምጦባት ፡ በዛች ፡ ውርንጩላ
ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ በክብር ፡ ሲገባ
ሆሳዕና ፡ ሲባል ፡ ሲዘመር ፡ ለክብሩ
ዘምባባው ፡ ሲነጠፍ ፡ ሁሉም ፡ ሆሆ ፡ እያሉ
ምትረግጠውን ፡ እንኳን ፡ ውርንጭላዪቱ
ያነጠፉላትን ፡ ሳይገባ ፡ ንጉሡ
ለእርሱ ፡ አይደል ፡ ቀርቶ ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ዉቀሳ??????
በፊት ፡ ማን ፡ አይቷታል ፡ ባለችበት ፡ ታስራ
እኛንም ፡ ኢየሱስ ፡ ከፈታልህ ፡ ክብሩን
ልቡ ፡ ከወደደህ ፡ ሊሰራብህ ፡ እርሱ
ጌታ ፡ መርጦን ፡ እንጂ ፡ ??? ፡ ተክቶልኛል
የማንጠቅም ፡ ባሪያዎች ፡ አይደለንም ፡ እኛ
አዝ:- ክብር ፡ ይሁን ፡ ለዝናው
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ዘለዓለም
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለተገባው (፪x)
ሁለት ፡ ባሮች ፡ ታግለው ፡ በጥንቱ ፡ ጨዋታ
አንደኛው ፡ ሲሸነፍ ፡ አንዱ ፡ ድል ፡ ሲነሳ
ህዝቡ ፡ ይነሳና ፡ ለአሸናፊው ፡ ጌታ
ይጨፍርለታል ፡ ባሪያው ፡ እየሰማ
ምንም ፡ ቢያሸንፍ ፡ ባሪያው ፡ በጉልበቱ
ጌታው ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ አድርጐታል ፡ የራሱ
እንዲህ ፡ ሲል ፡ ሰማሁት ፡ እንዲህ ፡ ሲል ፡ አምላኬ
ድል ፡ አድርጌያለሁኝ ፡ እኔማ ፡ በራሴ
ስለዚህ ፡ ስንኖር ፡ በዚህች ፡ ምድር ፡ ላይ
አምላክ ፡ እንዳለው ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ተወካይ
ስለእኛ ፡ ለሞተው ፡ ደግሞ ፡ ለተነሳው
የእርሱን ፡ ክብር ፡ አንጂ ፡ የእኛን ፡ ስራ ፡ እንርሳው???
አዝ:- ክብር ፡ ይሁን ፡ ለዝናው
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ዘለዓለም
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለተገባው (፪x)
|