ፍቅርህ ፡ በልቤ (Feqreh Belebie) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

()


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
ጨምሮ ፡ ፍቅርህ ፡ በልቤ ፡ ሲገባኝ ፡ የመወደዴ
ተራዬ ፡ ልኖር ፡ ለክብርህ ፡ ዘመኔን ፡ በቃ ፡ ልሰጥህ
የፍቅር ፡ ምላሼ ፡ ሊሆንህ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ ፡ ብዬ
እጆቼን ፡ አንስቼ ፡ መጣሁ ፡ እሄውልህ ፡ ውዴ
ተረቱን ፡ ተረቱን ፡ ንቄ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ስመጣ
አንተን ፡ አይቼ ፡ እንጂ ፡ ኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ፍለጋ (፭x)

አልገባኝም ፡ ነበር ፡ እኔ ፡ ያኔ ፡ ስትጠራኝ
እወድሃለሁ ፡ እኔ ፡ ስትለኝ ፡ መች ፡ እንዲህ ፡ መሰለኝ
ፊትህ ፡ ላይ ፡ እያነበብኩ ፡ ውዴ ፡ የፍቅር ፡ ፈገግታ
ኢየሱስዬ ፡ ብዬ ፡ ወዲያው ፡ እጄን ፡ እስካነሳ

አሳየኸኝ ፡ የፍቅር ፡ ፊትህን
መቼም ፡ ቢሆን ፡ እኔ አልለይህ
ኢሄውና ፡ መላ ፡ ማንነቴ
ንገሥበት ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ

አዝ:- ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ ኢየሱስ
በአንተ ፡ አይደል ፡ ይህን ፡ ክብር ፡ ያየሁት
በእኔ ፡ ላይ ፡ ልቤን ፡ ሌላ ፡ ትምከት
አይሞላም ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ አባት
የራሴ ፡ ትምክት ፡ እንዳይኖረኝ
ምህረትህ ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ አደረገኝ
ትላንትን ፡ ሳየው ፡ ዛሬ ፡ ሆኜ
አንተ ፡ ነህ ፡ እዚህ ፡ ለመድረሴ (፬x)

ለዓለም ፡ የቀረ ፡ ቦታ ፡ እስካይኖረኝ
የፍቅሬን ፡ በኩር ፡ እንካ ፡ የልቤን ፡ በኩር ፡ እንካ
ለራሴ ፡ የቀረ ፡ ቦታ ፡ እስካይኖረኝ
የፍቅሬን ፡ በኩር ፡ እንካ ፡ የልቤን ፡ በኩር ፡ እንካ
ለክብርህ ፡ የቀረ ፡ ቦታ ፡ እስካይኖረኝ
የክብሬን ፡ በኩር ፡ እንካ ፡ ውሰደው ፡ እንካ ፡ እንካ
የአንተ ፡ ነው ፡ እንካ ፡ እንካ ፡ ያነጠፍኩልህ ፡ እንካ
ተራመድበት ፡ እንካ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ናበት ፡ እንካ
ኦ ፡ የፍቅሬን ፡ በኩር ፡ እንካ ፡ ውሰደው (፬x)
 
አዝ:- (ውሰደው) ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ የኔ ፡ ኢየሱስ
(ውሰደው) በአንተ ፡ አይደል ፡ ይህን ፡ ክብር ፡ ያየሁት
(ውሰደው) በእኔ ፡ ላይ ፡ ልቤን ፡ ሌላ ፡ ትምከት
(ውሰደው) አይሞላም ፡ ኢየሱስ ፡ የኔ ፡ አባት
(ውሰደው) የራሴ ፡ ትምክት ፡ እንዳይኖረኝ
(ውሰደው) ምህረትህ ፡ እኔን ፡ ሰው ፡ አደረገኝ
(ውሰደው) ትላንትን ፡ ሳየው ፡ ዛሬ ፡ ሆኜ
አንተ ፡ ነህ ፡ እዚህ ፡ ለመድረሴ (፬x)