እንዳትሄድብኝ (Endathiedebegn) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
አዝ:- ህልውናህ ፡ ከሕይወቴ ፡ እንዳይሄድብኝ ፡ አሜን
መገኘትህ ፡ ከኑሮዬ ፡ እንዳይሄድብኝ ፡ አሜን
አብሮነትህ ፡ ከዘመኔ ፡ እንዳይሄድብኝ ፡ አሜን
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ከሕይወቴ ፡ እንዳትሄድብኝ ፡ አሜን
የኔ ፡ ክብር ፡ ከኑሮዬ ፡ እንዳትሄድብኝ ፡ አሜን
የኔ ፡ ሞገስ ፡ ከሕይወቴ ፡ እንዳትሄድብኝ ፡ አሜን

አንተ ፡ የተከልከው ፡ ከልብ ፡ የማይጠፋ
በውስጤ ፡ ረሃብ ፡ አለ ፡ ሚያስሮጠኝ ፡ አንተ ፡ ጋር
ባልደርስብህ ፡ እንኳን ፡ ያስቆምሃል ፡ ረሃቤ
ቀን ፡ ማታ ፡ እጮሃለሁ ፡ አትሂድብኝ ፡ ብዬ

ተናድጄ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
የምለምደው ፡ ሕይወት ፡ የለኝ ፡ እኔስ ፡ ሌላ
አያሽሽህ ፡ አያርቅህ ፡ማንነቴ
ታገስና ፡ እባክህ ፡ ኑር ፡ በሕይወቴ

እንዳትሄድብኝ ፡ ከሕይወቴ ፣ እንዳትሄድብኝ ፡ ከኑሮዬ (፪x)
እንዳትሄድብኝ ፡ እንዳትሄድብኝ (፬x)

አዝ:- ህልውናህ ፡ ከሕይወቴ ፡ እንዳይሄድብኝ ፡ አሜን
አባትዬ ፡ ከኑሮዬ ፡ እንዳትሄድብኝ ፡ አሜን
የኔ ፡ ክብር ፡ ከዘመኔ ፡ እንዳትሄድብኝ ፡ አሜን
እኔ ፡ አልችልም ፡ ያለ ፡ ክብርህ ፡ እንዳትሄድብኝ ፡ አሜን
መንፈስህን ፡ ከሕይወቴ ፡ አትውሰድብኝ ፡ አሜን
መገኘትህን ፡ ከኑሮዬ ፡ እንዳይሄድብኝ ፡ አሜን

የሰው ፡ ልጅ ፡ ሲያሳካ ፡ የዛሬው ፡ ጭንቀቱን
ይረሳዋል ፡ ደግሞ ፡ ሌላ ፡ ጥያቄውን
አንተ ፡ ግን ፡ ከጐደልክ ፡ ከሰው ፡ ልጅ ፡ ሕይወት
በምን ፡ ይረሳል ፡ ምን ፡ ያገኘ ፡ እለት

መልቶ ፡ ጌታ ፡ በእጄ ፡ ያለው ፡ የሰጠኅኝ
መቼም ፡ ቢሆን ፡ የአንተን ፡ ቦታ ፡ አይተካልኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የሸፈንከው ፡ ሰው ፡ አይወድቅም
ሁሉ ፡ ቀርቶ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እትሂድብኝ (እንዳትሄድብኝ)

እንዳትሄድብኝ ፡ ከሕይወቴ ፣ እንዳትሄድብኝ ፡ ከኑሮዬ (፪x)