ቸኮለብኝ (Chekolebegn) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
ሌላ ፡ ነገር ፡ ታገስ ፡ ብትለኝ
ጠብቃለሁ ፡ እስኪሆንልኝ
ግን ፡ አባቴ ፡ ለክብርህ ፡ ነገር
በህልውናህ ፡ ውሎ ፡ ለማደር

አዝ:- ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ልያዝህ
ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምሮቴ
አንተን ፡ ማየት ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ዓይኔ ፡ በርቶ ፡ አንዴ ፡ ልይህ
ኢየሱስ ፡ ውስጤ ፡ ራበኝ ፡ እስከምነካህ
ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ አልችልም ፡ መኖር ፡ ካለዚያ
ኢየሱስ ፡ በሌለበት ፡ ክብርህ ፡ ህልውናህ (፪x)

አዝ:- ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ልያዝህ
ናፍቆቴ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምሮቴ
አንተን ፡ ማየት ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ (፪x)

አንተን ፡ ማየት ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ
አባትዬ ፡ ፊትህ ፡ ጉጉቴ
ኢየሱሴ ፡ ክብርህ ፡ ጉጉቴ
አባትዬ ፡ ክብርህ ፡ ኢየሱሴ

ኢየሱሴ ፡ የነካው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ኢየሱሴ ፡ የገባው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ለሌላ ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)

የመቅደስን ፡ ደጅ ፡ የሚጠኑ
ብዙ ፡ ናቸው ፡ አንተን ፡ የሚሹ
አምላክህን ፡ አሳየኝ ፡ ሚሉኝ
ክብሩ ፡ የታል ፡ እስኪ ፡ አሳውቀን

ወዴት ፡ ልበል ፡ የት ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ ውዴ
በእኔ ፡ ዘመን ፡ ይረፍ ፡ ትውልዴ
ከእኔ ፡ ውጪ ፡ የትም ፡ አልጠቁም
በእኔ ፡ ላይ ፡ ና ፡ እስኪያይህ ፡ ሁሉም (፪x)

ኢየሱስ ፡ ዐይኔ ፡ በርቶ ፡ አንዴ ፡ ልይህ
ኢየሱስ ፡ ውስጤ ፡ ራበኝ ፡ እስከምነካህ
ኢየሱስ ፡ እኔ ፡ አልችልም ፡ መኖር ፡ ካለዚያ
ኢየሱስ ፡ በሌለበት ፡ ክብርህ ፡ ህልውናህ (፪x)

የጭንቅ ፡ ነው ፡ ስጠራህ ፡ ውዴ
የውስጤን ፡ ምጥ ፡ ቃላት ፡ ሰብስቤ
ቢነግርልኝ ፡ የልቤን ፡ ጩኸት
የጥማቴን ፡ የርሃቤን ፡ ልክ

እስከመቼ ፡ እንዲሁ ፡ በልማድ
ያሰለቻል ፡ ሲደገም ፡ ትላንት
ብዙ ፡ ክብር ፡ ብዙ ፡ ህልውና
አዲስነት ፡ በየማለዳ (፪x)

ኢየሱሴ ፡ የነካው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ኢየሱሴ ፡ የገባው ፡ ሰው
ኢየሱስን ፡ በዓይኑ ፡ ያየ ፡ ሰው
ለሌላ ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም
ለፈለገው ፡ ነገር ፡ መኖር ፡ አይችልም (፪x)