በድካሜ ፡ ማግስት (Bedekamie Magest) - ይድነቃቸው ፡ ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ፡ ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 1.jpeg


(1)

ቸኮለብኝ! ልቤ ፡ ሊያገኝህ
(Chekolebegn! Lebie Liyagegnh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

 
በድካሜ ፡ ማግስት ፡ ፊትህን ፡ ልይ ፡ አልል
ግን ፡ ውስጤ ፡ ናፍቆሃል ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልናገር
ፊትህ ፡ ተደፍቼ ፡ ማረኝ ፡ አልኩህና
ትቼዋለሁ ፡ አልከኝ ፡ ቀና ፡ እረከኝና
(፪x)

አቤቱ (፫x) ፡ እንደአንተ ፡ የሚገባው ፡ የለም
እንደ ፡ አንተ ፡ የሚሰማኝ ፡ የለም
እንደ ፡ አንተ ፡ የሚወደኝ ፡ የለም
እንደ ፡ አንተ ፡ ሚራራልኝ ፡ የለም (፪x)

በደል ፡ ፈጽሜ ፡ ፈርቼ
መንገድ ፡ ስጀምር ፡ ልሸሽ
ድንገት ፡ ናፍቀኀኝ ፡ መጥቼ
ድፍረቴን ፡ ሲነሳኝ ፡ ድካሜ

በእጆችህ ፡ የያዝከው (የያዝከው)
ምህረቴ ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ ያልከው
መለስካት ፡ ሕይወቴን ፡ ወደ ፡ አንተ (ወደ ፡ አንተ)
አልችልም ፡ በቃኝ ፡ ያለ ፡ አንተ

ፊትህን ፡ ከሰወርክብኝ ፡ ደነግጣለሁ
ዝም ፡ ካልከኝ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ጉድጓድ ፡ ምወርድ ፡ እመስላለሁ
ፈሪ ፡ ነኝ/እፈራለሁ ፡ ያለ ፡ ህልውናህ ፡ ውሎም ፡ ለማደር
በርትቼም ፡ ደክሜም ፡ ቢሆን ፡ ምርጫዬ ፡ እግርህ ፡ ስር (፪x)

በረሃ ፡ ላይ ፡ በጥም ፡ ለከሰለ
ፍቅርህን ፡ ተጠምቶ ፡ ለዛለ
አባት ፡ ከደጃፍ ፡ ቆመሃል
ልጅህን ፡ ለማየት ፡ ናፍቀሃል

ደፍሬ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ንቂ
ይሄውና ፡ እስከ ፡ ድካሜ
ያለ ፡ አንተ ፡ እንደማልችል ፡ አውቂ
ወጣሁኝ ፡ አባቴን ፡ ብዬ

ፊትህን ፡ ከሰወርክብኝ ፡ ደነግጣለሁ
ዝም ፡ ካልከኝ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ጉድጓድ ፡ ምወርድ ፡ እመስላለሁ
ፈሪ ፡ ነኝ/እፈራለሁ ፡ ያለ ፡ ህልውናህ ፡ ውሎም ፡ ለማደር
በርትቼም ፡ ደክሜም ፡ ቢሆን ፡ ምርጫዬ ፡ እግርህ ፡ ስር (፪x)

አቤቱ (፫x) ፡ እንደአንተ ፡ የሚገባው ፡ የለም
እንደ ፡ አንተ ፡ የሚሰማኝ ፡ የለም
እንደ ፡ አንተ ፡ የሚወደኝ ፡ የለም
እንደ ፡ አንተ ፡ ሚራራልኝ ፡ የለም