Yidnekachew Teka/Chekolebegn Lebie Liyagegneh/Bale Eda Negn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የደህንነቴ ፡ መደምደሚያ የክብር ፡ ስሜ ፡ ነህ ፡ መጠሪያ ማዕረጌ ፡ ሆነህ ፡ በሞትህ እኔም ፡ ተባልኩኝ ፡ ልጅህ (፪x)

የሞትህ ፡ ፍሬ ፡ የድካምህ በጣር ፡ የወለድከኝ ፡ ልጅህ በመከራ ፡ አልፈህ ፡ ያገኘኀኝ የዕንባህ ፡ ልጅህ ፡ ነኝ (፪x)

አዝ:- እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ፡ እኔ
የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ውለታህ ፡ ያለብኝ
እንዴት ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ነው
መክፈል ፡ የምችለው ፡ የፍቅርህን ፡ ሸክም
መቼም ፡ የማልመልሰው
ልክፈል ፡ እንኳን ፡ ብዬ ፡ ብጀምር ፡ ማለዳ
ፍቅርህን ፡ እንዲያው ፡ ሰጥተኀኛል
ታዲያ ፡ አይደለሁም ፡ ወይ ፡ የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ

መራመድ ፡ አይችሉም ፡ እግሮቼ ኢየሱስ ፡ በፍቅርህ ፡ ተይዤ እንዳልሄድ ፡ ከቶ ፡ ወደሌላ አርገኝ ፡ የፍቅርህ ፡ እስረኛ አርገኝ ፡ የፍቅርህ ፡ እስረኛ እንዳልሄድ ፡ ከቶ ፡ ወደሌላ ኢየሱስ ፡ በፍቅርህ ፡ ተይዤ መራመድ ፡ አይችሉም ፡ እግሮቼ

አዝ:- ንግሥና ፡ መጣ ፡ በደምህ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ክነቱም ፡ መጣ ፡ በሞት - ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ደህንነት ሆነ ፡ በጸጋ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ልጅ ፡ መባል ፡ ቢሆን ፡ በስራህ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ

እኔማ ፡ የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ የምህረትህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ መራመድ ፡ አልችልም ፡ እግሬ ተይዣለሁ ፡ እኔ

ነፍሱን ፡ ለወዳጁ ፡ ሚሰዋ
ይገኝ ፡ ይሆናል ፡ በመከራ
ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ ግን ፡ ሚገርመው
ለጠላትህ ፡ የሞትከው (፪x)

እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ የሚገዛ ልቤን ፡ የያዘ ፡ ውለታህ የፍቅር ፡ ዕዳ ፡ አኖርክብኝ ሳልወድህ ፡ ወደድከኝ (፪x)

አዝ:- መልክህና ፡ ውበትህ ፡ ጠፋ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
በሰው ፡ ተንቀህ ፡ ተጠላህ - ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ተፈወስኩኝ ፡ አንተ ፡ ቆስለህ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ደዌ ፡ ህመሜን ፡ ወሰድህ - ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ

</poem> }}