ላመሰግንህ (Lameseginih) - ያሬድ ፡ ማሩ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ያሬድ ፡ ማሩ
(Yared Maru)

Lyrics.jpg


(Volume)

Fikereh Yasgeremegnal
(ፍቅርህ ፡ ያስገርመኛል)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፪ ((2012))
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6ː26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የያሬድ ፡ ማሩ ፡ አልበሞች
(Albums by Yared Maru)

ሚስኪኑን ፥ ጠራኀኝና ፥ እና ኣበሳን ከእኔ ኣራክና
ኣፌን ለምስጋና ከፈትከው ስለዚህ አዘምራለው
ውድቀቴን ለፍጥረት ሊያውጅ መለከቱንም ሲያዘጋጅ
በጠላቴ ፊት ቀባኀኝ ከፍታውን አስረገትከኝ

ላመሰግንህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ዘመን ከመጣልኝ
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነለኝ እጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭)

መቆዘም ከእንግዲህ ቀረ ጠላቴም ይኸው አፈረ
በኮረብታ ላይ ቆሜአለሁ ምስጋናዬን አሰማለሁ
ተራሮችም አስተጋቡ ምስጋናዬንም አጀቡ
እናንተንም ከእኔ ጋራ ዘምሩ ስራው ይውራ

ላገለግልህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ቃልህ ከመጣልኝ
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነልኝ አጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭)

ገበታ ተዘጋጀልኝ ረሃቤንም እረሳሁኝ
ጽዋዬም የተረፈ ነው ዛሬ ለሌሎች ሆኛለሁ(፪)

ላመሰግንህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ዘመን ከመጣልኝ
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነልኝ አጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭)

ባለቀሱኩባቸው ቀኖች ፈንታ ደስታ ሆኖልኛል ባንተ ጌታ (፫)
በቆዘምኩባቸው ወራት ፈንታ እረፍት ከበበኝ የእኔ ጌታ (፫)
ውድቀቴን በሚሻ ጠላቴ ፊት እራሴን ቀባኸው በዘይት (፫)

ዛሬም ላመስግንህ በደስታ ስራዬን ሰርተሃል ጌታ (፬)
ላመሰግንህ ተራው ከደረሰኝ መቆዘም ቀርቶ ዘመን ከመጣልኝ
ከፍታን መውረስ ባንተ ከሆነልኝ አጆቼን ላንሳ ጌታ ክበርልኝ (፭)