ታላቅና ፡ የተፈራህ (Talaqena Yeteferah) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 1.jpg


(1)

ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
(Kesat West Yeneteqegn)

ዓ.ም. (Year): ዓ.ም. (Year)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

እልፍ ፡ አእላፋት ፡ መላዕክት ፡ ከፊትህ ፡ እየሰገዱ
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያሉ ፡ ሁሌ ፡ የሚያመልኩህ
በረከትና ፡ ክብር ፡ ምሥጋናም ፡ ሃይልም
ለአንተ ፡ ለቅዱሱ ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም

አዝ፦ ታላቅና ፡ የተፈራህ ፡ አምላክ
በቅድስናህ ፡ የከበርህ ፡ ጌታ
ከፍ ፡ ካለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ በከፍታ ፡ ያለህ
ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ታላቁ ፡ ስምህ ፡ ይክበር

ከዘመናት ፡ ሁሉ ፡ ክብርህን ፡ ጠብቀህ
ሳትሻር ፡ ሳትለወጥ ፡ በዙፋንህ ፡ ጸንተህ
ያለህና ፡ የነበርህ ፡ ሁሉን ፡ ምትገዛ ፡ አምላክ
በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ክቡር ፡ ስምህ ፡ ይባረክ

አዝ፦ ታላቅና ፡ የተፈራህ ፡ አምላክ
በቅድስናህ ፡ የከበርህ ፡ ጌታ
ከፍ ፡ ካለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ በከፍታ ፡ ያለህ
ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ታላቁ ፡ ስምህ ፡ ይክበር

ማለዳ ፡ እጅግ ፡ ተሞልቶ ፡ ከክብርህ ፡ ታላቅነት
አምልኮ ፡ ለአንተ ፡ ይቀርባል ፡ ዘወትር ፡ ቀንና ፡ ሌሊት
ሃያልና ፡ ባለብዙ ፡ ግርማ ፡ ሞገስ
እንደአንተ ፡ የለምና ፡ ለዘለዓለም ፡ ንገሥ

አዝ፦ ታላቅና ፡ የተፈራህ ፡ አምላክ
በቅድስናህ ፡ የከበርህ ፡ ጌታ
ከፍ ፡ ካለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ በከፍታ ፡ ያለህ
ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ታላቁ ፡ ስምህ ፡ ይክበር

ልጽሆም ፡ ልጽህር ፡ የፈቀድከውን ፡ ልታደርግ
ሃይልና ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ፡ የወሰንከውን ፡ ልትፈጽም
አማካሪና ፡ ረዳት ፡ ከቶ ፡ የማያስፈልግህ
ምንም ፡ የማይጐድልህ ፡ ፍፁም ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ

አዝ፦ ታላቅና ፡ የተፈራህ ፡ አምላክ
በቅድስናህ ፡ የከበርህ ፡ ጌታ
ከፍ ፡ ካለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ በከፍታ ፡ ያለህ
ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ታላቁ ፡ ስምህ ፡ ይክበር