From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አቤቱ ፡ ፈውሰን ፡ እኛም ፡ እንፈወሳለን
አቤቱ ፡ መልሰን ፡ እኛም ፡ እንመለሳለን (፪x)
ቃልኪዳንና ፡ ሚሉትን ፡ የምትጠብቅ
ታላቅና ፡ ሃያል ፡ የተፈራህ ፡ አምላክ
በደረሰብን ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ አንተ ፡ ጻዲቅ ፡ ነህ
ቤትህን ፡ መልስልን ፡ ጉስቁልናችንን ፡ አይተህ
አዝ፦ አቤቱ ፡ ፈውሰን ፡ እኛም ፡ እንፈወሳለን
አቤቱ ፡ መልሰን ፡ እኛም ፡ እንመለሳለን (፪x)
እንደበደላችን ፡ አታድርግብን
እንደኀጢአታችንም ፡ አትክፈለን
እጠበን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኛም ፡ እንነጻለን
ከበረዶ ፡ ይልቅ ፡ ነጭ ፡ እንሆናለን
አዝ፦ አቤቱ ፡ ፈውሰን ፡ እኛም ፡ እንፈወሳለን
አቤቱ ፡ መልሰን ፡ እኛም ፡ እንመለሳለን (፪x)
በብዙ ፡ እንግዳ ፡ ነገር ፡ ረክሰናል
የተወደደው ፡ እርሻ ፡ በባሕር ፡ ተረግጧል
ጠላትም ፡ በቤትህ ፡ ጓዳ ፡ ይኖራል
የተቀደሰው ፡ እቃ ፡ ለብዝበዛ ፡ ሆኗል
አዝ፦ አቤቱ ፡ ፈውሰን ፡ እኛም ፡ እንፈወሳለን
አቤቱ ፡ መልሰን ፡ እኛም ፡ እንመለሳለን (፪x)
ከአመጻችን ፡ ብዛት ፡ መንፈስህን ፡ አስመረርን
እጅግ ፡ አስቆጣንህ ፡ በእምቢተኝነታችን
አንተ ፡ ግን ፡ ምህረትህ ፡ የበዛ ፡ አምላክ ፡ ነህ
ታደገን ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ ስለስምህ ፡ ብለህ
አዝ፦ አቤቱ ፡ ፈውሰን ፡ እኛም ፡ እንፈወሳለን
አቤቱ ፡ መልሰን ፡ እኛም ፡ እንመለሳለን (፪x)
|