ነፍሴ ፡ ሆይ (Nefsie Hoy) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 1.jpg


(1)

ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
(Kesat West Yeneteqegn)

ዓ.ም. (Year): ዓ.ም. (Year)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

"የአብርሃም ፡ የይሳቅ ፡ የያዕቆብ ፡ አምላክ
ዛሬም ፡ በቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ አለና
ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ በፊቱ ፡ ዝም ፡ ይበል
እግዚአብሔር ፡ አለና ፡ እግዚአብሔር ፡ አለና"

አዝ፦ የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ ፡ ለዘለዓለምም ፡ ነዋሪ
ማይደክም ፡ ማይታክተው ፡ ማስተዋሉ ፡ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በከፍታው

ልደካማ ፡ ሃይልን ፡ ይሰጣል
ጉልበት ፡ ላጣው ፡ ብርታት ፡ ይጨምራል
በጽድቁ ፡ ቀን ፡ ደግፎ ፡ ይይዛል
እግዚአብሔር ፡ ህዝቡን ፡ መቼ ፡ ይተዋል (፪x)

አዝ፦ የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ ፡ ለዘለዓለምም ፡ ነዋሪ
ማይደክም ፡ ማይታክተው ፡ ማስተዋሉ ፡ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በከፍታው

ወፎችን ፡ በእፍኙ ፡ የሰፈረው
ሰማይን ፡ በስንዝር ፡ የለካው
ከፍ ፡ ባለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው
ለትውልድ ፡ ሁሉ ፡ መጠጊያ ፡ ነው

አዝ፦ የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ ፡ ለዘለዓለምም ፡ ነዋሪ
ማይደክም ፡ ማይታክተው ፡ ማስተዋሉ ፡ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በከፍታው

ስለደሆች ፡ መከራ ፡ ስለችግረኞች
ጌታዬ ፡ ይመጣል ፡ ወደመቅደሱ ፡ በድንገት
የወደቀ ፡ ይነሳል ፡ የሳት ፡ ይመለሳል
በግዚአብሄር ፡ ጉብኝት ፡ ገና ፡ ጠላት ፡ ይቃጠላል

ተስፋ ፡ የቆረጣችሁ ፡ በእምነት ፡ የደክማችሁ
በጠላትም ፡ ዛቻ ፡ አንገት ፡ የደፋቹህ
አምላካቹህ ፡ በበቀል ፡ በእርግጥ ፡ ይመጣል
የእናንተም ፡ ደስታ ፡ ገና ፡ ከሩቅ ፡ ይሰማል

ያዕቆብ ፡ ሆይ ፡ እስራኤልም ፡ ሆይ
አልሰማህም ፡ ወይ ፡ አላወቅህም ፡ ወይ (፪x)

መንገዴ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ተሰውራለች
ፍርዴም ፡ ከአምላኬ ፡ ደግሞም ፡ አልፋለች
ለምን ፡ ትላለህ ፡ ለምንስ ፡ እንዲህ ፡ ትናገራለህ
አልሰማህም ፡ ወይ ፡ አላወቅህም ፡ ወይ

የኛ ፡ ጌታ ፡ አለ (አለ) ፡ እንደነገሠ (አለ)
አላረጀም (አለ) ፡ አልደከመም (አለ)
አይታክትም (አለ) ፡ አለ ፡ ጌታ (አለ)
አለ ፡ ጌታ (አለ) ፡ ትላንትናም ፡ ዛሬ (አለ)
ነገም ፡ ለዘለዓለም (አለ) ፡ ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (አለ)
አለ ፡ ጌታ (አለ) ፡ አለ ፡ ጌታ ፡
አለ ፡ ውዴ (አለ) ፡ አለ ፡ ጌታ (አለ)