ሃሌሉያ (Hallelujah) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 1.jpg


(1)

ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
(Kesat West Yeneteqegn)

ዓ.ም. (Year): ዓ.ም. (Year)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

አዝሃሌሉያ (፬x)
ከኀጢአት ፡ ባርነት ፡ ከዘለዓለም ፡ ሞት
አዳነን ፡ ኢየሱስ ፡ እኛን ፡ ሰጠን ፡ ሕይወት

ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ሲሆን ፡ እራሱን ፡ አዋረደ
የባሪያውን ፡ መልክ ፡ ይዞ ፡ ከሰማይ ፡ ወረደ
በጠና. (1) . ፡ ከስፍራው ፡ በበረት ፡ ተወለደ
ስለኀጢአተኞች ፡ ስለእኛ ፡ ማለደ

አዝሃሌሉያ (፬x)
ከኀጢአት ፡ ባርነት ፡ ከዘለዓለም ፡ ሞት
አዳነን ፡ ኢየሱስ ፡ እኛን ፡ ሰጠን ፡ ሕይወት

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ለመሞት ፡ ፈቃደኛውን
ከዘለዓለም ፡ ሞት ፡ ሊያድንን ፡ ከኩነኔ
የጥልቅ ፡ ግድግዳውን ፡ በሥጋው ፡ አፈረሰ
ለኀጢአት ፡ ይቅርታ ፡ ደሙን ፡ አፈሰሰ

አዝሃሌሉያ (፬x)
ከኀጢአት ፡ ባርነት ፡ ከዘለዓለም ፡ ሞት
አዳነን ፡ ኢየሱስ ፡ እኛን ፡ ሰጠን ፡ ሕይወት

ሰላሳ ፡ ሶስት ፡ አመት ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኖረ
የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ ለሰዎች ፡ አስተማረ
የሁሎችን ፡ በደል ፡ እርሱ ፡ ተሸከመ
አገልግሎቱን ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ፈጸመ

አዝሃሌሉያ (፬x)
ከኀጢአት ፡ ባርነት ፡ ከዘለዓለም ፡ ሞት
አዳነን ፡ ኢየሱስ ፡ እኛን ፡ ሰጠን ፡ ሕይወት