From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ጌታ ፡ ያየለትን ፡ ሳይወርስ ፡ አይመለስም (፪x)
የሕያው ፡ አምላክ ፡ ጭፍራ ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ አይቀርም (፪x)
ሙዋርትኞቹ ፡ ሟርት ፡ በእስራኤል ፡ ላይ ፡ አይሰራም
አስማትም ፡ በያቆብ ፡ ላይ ፡ የለም (፪x)
አዝ፦ ገና ፡ እንወርሳለን ፡ ገና
ከእግዚአብሄር ፡ አፍ ፡ ቃል ፡ ወጥቷልና (፪x)
ከህልሙ ፡ የሚያኑን??? ፡ እናያለን ፡ ያሉ (፪x)
እየተዘባበቱ ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ የጣሉት (፪x)
ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ ፡ ብለው ፡ እስኪያወሩ (፪x)
አምላኬ ፡ አሳያቸው ፡ በድንቅ ፡ አሰራሩ (፪x)
ቀስተኞች ፡ ቢያስቸግሩትም
ቢነድፉት ፡ እጅጉም ፡ ቢቃወሙትም
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ክንድ ፡ አበረታ
በመከራ ፡ አገር ፡ አፈራው
በወንዶችና ፡ በሴቶች ፡ ባሪያዎቹ ፡ ላይ
በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ ላይ
አምላኬ ፡ ያፈሳል ፡ መንፈሱን ፡ ከሰማይ (፪x)
በነብዩ ፡ በእዩኤል ፡ የተባለዉ
የተስፋው ፡ ቃል ፡ ለእኛም ፡ ነው
አዝ፦ ገና ፡ እንወርሳለን ፡ ገና
ከእግዚአብሄር ፡ አፍ ፡ ቃል ፡ ወጥቷልና (፪x)
ከህልሙ ፡ የሚሆነውን ፡ እናያለን ፡ ያሉ (፪x)
እየተዘባበቱ ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ የጣሉት (፪x)
ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ ፡ ብለው ፡ እስኪያወሩ (፪x)
አምላኬ ፡ አሳያቸው ፡ በድንቅ ፡ አሰራሩ (፪x)
ቀስተኞች ፡ ቢያስቸግሩትም
ቢነድፉት ፡ እጅጉም ፡ ቢቃወሙትም
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ክንድ ፡ አበረታ
በመከራ ፡ አገር ፡ አፈራው
አዝ፦ ገና ፡ እንወርሳለን ፡ ገና
ከእግዚአብሄር ፡ አፍ ፡ ቃል ፡ ወጥቷልና (፪x)
እጅ ፡ የምታህል ፡ ትንሽ ፡ ደመና
ብታዩ ፡ ዝናቡ ፡ እጅግ ፡ ነውና (፪x)
በጊዜው ፡ የሚፈጸመውን ፡ ቃል
የሰማ ፡ ለክብሩ ፡ አሜን ፡ ይበል
በጊዜው ፡ የሚፈጸመውን ፡ ቃል
የሰማ ፡ በደስታ ፡ እሰይ ፡ ይበል
የዘንዶ ፡ ራስ ፡ ተቀጥቅጦ
የእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ በኢትዮፕያ ፡ በሙላት ፡ ተገልጦ
አዝ፦ ገና ፡ እናያለን ፡ ገና
ከእግዚአብሄር ፡ አፍ ፡ ቃል ፡ ወጥቷልና (፪x)
ገና ፡ እንወርሳለን ፡ ገና
ከእግዚአብሄር ፡ አፍ ፡ ቃል ፡ ወጥቷልና (፪x)
ገና ፡ እናያለን ፡ ገና
ከእግዚአብሄር ፡ አፍ ፡ ቃል ፡ ወጥቷልና (፪x)
|