እግዚአብሔር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ባይሆን ፡ ኖሮ (Egziabhier Kenie Gar Bayhon Noro) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 1.jpg


(1)

ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
(Kesat West Yeneteqegn)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ባይሆን ፡ ኖሮ ፡ በእነዚህ ፡ ዓመታት
በክንዱ ፡ ደግፎ ፡ ባያሻግረኝ ፡ ክፉዎቹን ፡ ቀናት
አጠገቤ ፡ ቆሞ ፡ ባያበረታኝ ፡ በነውጡ ፡ ሰዓት
ሕያው ፡ ሳለሁኝ ፡ በዋጠኝ ፡ ነበር ፡ ጠላቴ ፡ እንደቁጣው ፡ ጽናት (፪x)

የአመጽን ፡ ፈሳሽ ፡ እያደረቀ ፡ የጥፋትን ፡ ጎርፍ ፡ እየገደበ
ነፍሴን ፡ እንደወፍ ፡ ከአዳኞች ፡ ወጥመድ ፡ እያስመለጣት
ላኖረኝ ፡ ጌታ ፡ እስቲ ፡ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዋዕት

(ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ልመናዬን ፡ ሰማኝ
ከላይ ፡ ከመቅደሱ ፡ ረድኤቱን ፡ ላከልኝ
የጠላቶቼን ፡ ከፍታ ፡ አስረገጠኝ
በማዳኑ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ
(፪x)

(ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

ለጥርሱ ፡ ንክሻ ፡ አላደረገኝ
ከተደበቀብኝ ፡ ወጥመድ ፡ አዳነኝ
ነፍሴን ፡ ከመከራ ፡ ሁሉ ፡ ላዳናት
ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡ ዘሬም ፡ ይገዛለት
(፪x)

(ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

ምንም ፡ ያህል ፡ ብዙ ፡ ወዳጆች ፡ ቢኖሩም
በመከራ ፡ ቀን ፡ ግን ፡ ማንም ፡ አይገኝም
ፍፁም ፡ ሳይለወጥ ፡ ልመናን ፡ ሚፈጽም
ታማኙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም
ፊቱ ፡ ሳይቀየር ፡ ልመናን ፡ ሚፈጽም
ታማኙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይክበር ፡ ለዘለዓለም

(ሃሌሉያ) ሃሌሉ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

የተግሳጽና ፡ የዘለፋው ፡ ብዛት
አቤት ፡ በመከራ ፡ ቀን ፡ የተግዳሮት ፡ አይነት
የጠላትን ፡ ትዕቢት ፡ የጨለማውን ፡ ብርታት
በአንዲት/በአፉ ፡ ቃል ፡ ሽሮ ፡ ያከብራል ፡ በቅጽበት
(፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ባይሆን ፡ ኖሮ ፡ በእነዚህ ፡ ዓመታት
በክንዱ ፡ ደግፎ ፡ ባያሻግረኝ ፡ ክፉዎቹን ፡ ቀናት
አጠገቤ ፡ ቆሞ ፡ ባያበረታኝ ፡ በነዉጡ ፡ ሰዓት
ሕያው ፡ ሳለሁኝ ፡ በዋጠኝ ፡ ነበር ፡ ጠላቴ ፡ እንደቁጣው ፡ ጽናት (፪x)

የአመጽን ፡ ፈሳሽ ፡ እያደረቀ ፡ የጥፋትን ፡ ጎርፍ ፡ እየገደበ
ነፍሴን ፡ እንደወፍ ፡ ከአዳኞች ፡ ወጥመድ ፡ እያስመለጣት
ላኖረኝ ፡ ጌታ ፡ እስቲ ፡ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዋዕት

(ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉያ
(ኦ ፡ ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ