From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የአብርሃም ፡ የይስሃቅ ፡ የያዕቆብ ፡ አምላክ
ዛሬም ፡ በቅዱስ ፡ ማደሪያው ፡ አለና
ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ በፊቱ ፡ ዝም ፡ ይበል
እግዚአብሔር ፡ አለና
አዝ፦ የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ
ለዘለዓለምም ፡ ነዋሪ
ማይደክም ፡ ማይታክተዉ
ማስተዋሉ ፡ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በከፍታው
ለደካማ ፡ ኃይልን ፡ ይሰጣል
ጉልበት ፡ ላጣው ፡ ብርታት ፡ ይጨምራል
በጽድቁ ፡ ቀን ፡ ደግፎ ፡ ይይዛል
እግዚአብሔር ፡ ህዝቡን ፡ መቼ ፡ ይተዋል (፪x)
አዝ፦ የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ
ለዘለዓለምም ፡ ነዋሪ
ማይደክም ፡ ማይታክተዉ
ማስተዋሉ ፡ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በከፍታው
ወፎችን ፡ በእፍኙ ፡ የሰፈረ
ሠማይን ፡ በስንዝር ፡ የለካዉ
ከፍ ፡ ባለ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው
ለትውልድ ፡ ሁሉ ፡ መጠጊያ ፡ ነው
አዝ፦ የምድር ፡ ዳርቻ ፡ ፈጣሪ
ለዘለዓለምም ፡ ነዋሪ
ማይደክም ፡ ማይታክተዉ
ማስተዋሉ ፡ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በማደሪያው
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በከፍታው
ስለድሆች ፡ መከራ ፡ ስለችግረኞች
ጌታዬ ፡ ይመጣል ፡ ወደመቅደሱ ፡ በድንገት
የወደቀ ፡ ይነሳል ፡ የሳተ ፡ ይመለሳል
በእግዚአብሔር ፡ ጉብኝት ፡ ገና ፡ ጠላት ፡ ይቃጠላል
ተስፋ ፡ የቆረጣችሁ ፡ በእምነት ፡ ደክማችሁ
በጠላትም ፡ ዛቻ ፡ አንገት ፡ የደፋቹህ
አምላካቹህ ፡ በበቀል ፡ በእርግጥ ፡ ይመጣል
የእናንተም ፡ ደስታ ፡ ገናስ ፡ ከሩቁ ፡ ይሰማል
ያዕቆብ ፡ ሆይ ፡ እስራኤልም ፡ ሆይ
አልሰማህም ፡ ወይ ፡ አላወቅክም ፡ ወይ (፪x)
መንግዴ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ተሰውራለች
ፍርዴም ፡ ከአምላኬ ፡ ደግሞም ፡ አልፋለች
ለምን ፡ ትላለህ ፡ ለምንስ ፡ እንዲህ ፡ ትናገራለህ
አልሰማህም ፡ ወይ ፡ አላወክህም ፡ ወይ
የእኛ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ (አለ) ፡ እንደነገሠ ፡ (አለ)
አላረጀም ፡ (አለ) ፡ አልደከመም ፡ (አለ)
አይታክትም ፡ (አለ) ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ (አለ)
አለ ፡ ጌታ ፡ (አለ) ፡ ትናንትናም ፡ ዛሬም ፡ (አለ)
ነገም ፡ ለዘለዓለም ፡ (አለ) ፡ ያው ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (አለ)
አለ ፡ ጌታ ፡ (አለ) ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ (አለ)
አለ ፡ ውዴ ፡ (አለ) ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ (አለ ፡ አለ)
|