በውኃ ውስጥ ፡ አልፈናል (Beweha West Alfenal) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 1.jpg


(1)

ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ የነጠቀኝ
(Kesat West Yeneteqegn)

ዓ.ም. (Year): ዓ.ም. (Year)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

አዝ፦ በውኃ ውስጥ ፡ አልፈናል ፡ አላሰጠመንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሄደናል ፡ አላቃጠለንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
ባለፍንበት ፡ መንገድ ፡ የጠበቀን
ያሻገረን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
እስከዚች ፡ ቀን ፡ ድረስ ፡ የጠበቀን
የደረሰልን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገንልን

በሁሉ ፡ ላይ ፡ ስልጣን ፡ ያለው ፡ ጌታ
በቃልህና ፡ በስራህ ፡ የበረታህ
በጉልበቱ ፡ ጽናት ፡ የሚራመድ
ጥልቁን ፡ ባሕር ፡ አረገልን ፡ መንገድ
ያንን ፡ ባሕር ፡ አደረገልን ፡ መንገድ

አዝ፦ በውኃ ውስጥ ፡ አልፈናል ፡ አላሰጠመንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሄደናል ፡ አላቃጠለንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
ባለፍንበት ፡ መንገድ ፡ የጠበቀን
ያሻገረን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
እስከዚች ፡ ቀን ፡ ድረስ ፡ የጠበቀን
የደረሰልን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገንልን

ምንም ፡ ያህል ፡ እሳት ፡ ቢነድም
የመከራ ፡ እቶን ፡ ቢያይልም
እግዚአብሔር ፡ የተባዥው
አስተማማኝ ፡ ማምለጫ ፡ አለው
አስተማማኝ ፡ ማለፊያ ፡ አለው

አዝ፦ በውኃ ውስጥ ፡ አልፈናል ፡ አላሰጠመንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሄደናል ፡ አላቃጠለንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
ባለፍንበት ፡ መንገድ ፡ የጠበቀን
ያሻገረን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
እስከዚች ፡ ቀን ፡ ድረስ ፡ የጠበቀን
የደረሰልን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገንልን

እንደአገኘን ፡ መከራ ፡ ብዛት
እንደነደደው ፡ እሳት ፡ ብርታት
እስከዛሬ ፡ ዘር ፡ ባልቀረልን
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ይልቅ ፡ አበዛን
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ በጤና ፡ አኖረን

አዝ፦ በውኃ ውስጥ ፡ አልፈናል ፡ አላሰጠመንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ሄደናል ፡ አላቃጠለንም
ኦ ፡ ይገርማል ፡ ኦ ፡ ይደንቃል
ባለፍንበት ፡ መንገድ ፡ የጠበቀን
ያሻገረን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
እስከዚች ፡ ቀን ፡ ድረስ ፡ የጠበቀን
የደረሰልን ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገንልን