የሚበልጠው ፡ መንገድ (Yemibeltew Menged) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 2.jpeg


(2)

አመልከዋለሁ
(Amelkewalehu)

ዓ.ም. (Year): (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

ሥራችንን ፡ ለእሳት ፡ መቃጠል ፡ አሳልፈን ፡ ብንሰጥም
በመልአክት ፡ ልሳን ፡ እንኳን ፡ ብንናገርም
ተራሮችን ፡ እስከናፈርስ ፡ እምነት ፡ ቢኖረንም
ፍቅር ፡ ግን ፡ ከሌለን ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ አይጠቅምም

አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ
ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ : እንሂድ (፪x)

አንዲያ ፡ ልጁን ፡ እስኪሰጠን ፡ ድረስ ፡ ከወደደን
በደላችንን ፡ ሳይቆጥር ፡ ከእራሱ ፡ ጋር ፡ ካስታረቀን
ከወንድማማች ፡ መዋደድ ፡ ነፍሳችንንም ፡ አጥተን
እንጓዝ ፡ ከሁሉ ፡ በሚበልጠው ፡ መንገድ ፡ እያስተዋልን

አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ
ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x)

በፍቅር ፡ የሚኖር ፡ በእግዚአብሔር ፡ ይኖራል
በእግዚአብሔርም ፡ በእርሱ ፡ ኑሮና ፡ ህይወት ፡ ይታያል
ጌታ ፡ ለእርሱ ፡ ያለውን ፡ ፍቅር ፡ ያወቀ ፡ ቢኖር
ባለ ፡ እንጀራውን ፡ እንደራሱ ፡ ይውደድ ፡ በደልን ፡ አይቁጠር

አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ
ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x)

ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ማለትን ፡ መተጣጠብ ፡ ሲኖር
በፍቅር ፡ አንዱ ፡ ለሌላው ፡ እራሱን ፡ ማስገዛት ፡ ሲጀምር
አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ ውበቱ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ መዓዛው
ፍቅር ፡ ነውና ፡ የርስቱ ፡ ዋና ፡ መለያው

አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ
ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x)

ባለእንጀራችንን ፡ እንደ ፡ እራሳችን ፡ እንውደድ
ድካሙን ፡ እያየን ፡ በድፍረት ፡ አንፍረድ
እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነውና ፡ በፍቅር ፡ እንኑር
ይሄ ፡ ነው ፡ መታወቂያው ፡ የጌታ ፡ ደቀመዝሙር

አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ
ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x)

ለእግዚአብሔር ፡ ያለን ፡ ፍቅር ፡ የሚረጋገጠው
በአጠገባችን ፡ ያለውን ፡ ወንድማችንን ፡ ስንወደው ፡ ነው
ጌታ ፡ ደስ ፡ በሎት ፡ መስዕዋታችንን ፡ የሚያሸተው
በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል ፡ ጥሩ ፡ ልብ ፡ ሲኖረን ፡ ነው

አዝ፦ ከሁሉ ፡ የሚበልጠዉ ፡ መንገድ ፡ መንገድ
ፍቅር ፡ ነውና ፡ በእርሱ ፡ እንሂድ ፡ (፪x)