ፀሎቴን ፡ ቢከለክልም (Tselotien Bikelekelem) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 2.jpeg


(2)

አመልከዋለሁ
(Amelkewalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

ቢያሳዝንም ፡ እንደምሕረቱ ፡ ብዛት ፡ ይራራልና
የሰውን ፡ ልጆች ፡ ከልቡ ፡ አያስጨንቅምና
አፌን ፡ በአፈር ፡ ውስጥ 2x አኖራለው
ዝም ፡ ብዬ ፡ ማዳኑን ፡ ተስፋ ፡ አደርጋለው

እግዛብሄር ፡ የታመነ ፡ ነው 3x
ጌታዬ ፡ ለዘላለም ፡ አይጥልም

ጸሎቴን ፡ ቢከለክልም ፡ ጩህቴን ፡ ባይሰማ
ልመናን ፡ ሳበዛ ፡ ፊቱን ፡ ከእኔ ፡ ቢሰውርም

መንገዴን ፡ እስቲ ፡ ልመርምር
ወደ ፡ እግዛብሄር ፡ ልመለስ
ልቤን ፡ ከእጄ ፡ ጋር ፡ በሰማይ ፡ ወደለው ፡ ላንሳ
በሃጥያቴ ፡ ቢቆጣም ፡ እንኳ ፡ ስለዓመጻዬም ፡ ቢቀጣኝም
እግዛብሄር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ፍጽሞ ፡ አይተወኝም

ከሰማይ ፡ እስኪጐበኘኝ ፡ እስኪመለከተኝ ፡ ድረስ
ዓይኔ ፡ ሳታቋርጥ ፡ እምባዬን ፡ ታፍስስ ፡ ታፍስስ
በጥቂት ፡ ቁጣ ፡ ፊቱን ፡ ከእኔ ፡ ቢሰውርም
በዘላለም ፡ ቸርነት ፡ ይምራል ፡ እግዚአብሔር