From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ ሊተካው
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው
ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x)
መናወጥ ፡ ከሞላበት ፡ የምጥ ፡ ዘመን
የእራሱ ፡ በቂ ፡ የሆነ ፡ ክፋት ፡ ያለበት
ነፍሴን ፡ ከሚያስጨንቅ ፡ ዕለት ፡ ዕለት
መኖሪያዬ ፡ ኢየሱስን ፡ የዘለዓለም ፡ ማለት
አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ የሚተካው
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው
ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x)
እራሱን ፡ ሊገልጥ ፡ ወዶ ፡ ያደረገው
የሕይወት ፡ መንገድ ፡ ትግል ፡ የበዛው
ክፉዉን ፡ ለበጐ ፡ የለወጠው
አምላኬ ፡ በጥበቡ ፡ አሳመረው
አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ የሚተካው
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው
ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x)
በማልመርጠው ፡ መንገድ ፡ ሲማራኝ
ለካስ ፡ ውዴ ፡ በሕይወት ፡ ሲጠብቀኝ
ልመናዬ ፡ ዝብዘባዬ ፡ ሳያውከው
መልካሙን ፡ ዘምን ፡ ለእኔ ፡ አቆየው
አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው
ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ የሚተካው
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው
ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x)
|