From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ደረት ፡ እየደቁ ፡ የተከተሉትን
"እናንተ ፡ የኢየሩሳሌም ፡ ሴቶች ፡ ለራሳችሁ ፡ አልቅሱ" ፡ ብሎ ፡ መልሶ
የተዘባበቱበትንም ፡ ሁሉ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ጭምር ፡ ታግሶ
የመዳናችንም ፡ ራስ ፡ በመከራ ፡ የፈጸመውን ፡ ጌታ ፡ ተመልክተን
በተሰጠን ፡ ፀጋ ፡ በታማኝነት ፡ ለማገልገል ፡ እንበርታ
አዝ፦ እንደ ፡ ተሰጠህ ፡ አገልግል
ከሠማይ ፡ የሆነውን ፡ አደራ ፡ ችላ ፡ አትበል
ከሚያገሰግኑ ፡ አፍ ፡ እንዳትፈተን ፡ ልብህን ፡ አትጣ
በተቃዋሚዎችም ፡ ተደናግጠህ ፡ ፈቀቅ ፡ እንዳትል
የጠራህን ፡ ጌታ ፡ እያየህ ፡ ሩጫውን ፡ ቀጥል
ከአፉ ፡ የሚወጣው ፡ ቃል ፡ ይሁን ፡ መኖሪያ
የተጻፈው ፡ ለትምህርት ፡ ይሁን ፡ መመሪያ
የላከህ ፡ ያለህን ፡ ሁሉ ፡ ያደረገ
ዳግመኛ ፡ ሲመለስ ፡ ጌታ ፡ እንዲያገኝህ
የጊዜው ፡ ስካር ፡ ከዓላማህ ፡ እንዳያስትህ
ንቃ ፡ ተጠበቅ ፡ አደራ ፡ እንዳያስጥል
አዝ፦ እንደ ፡ ተሰጠህ ፡ አገልግል
ከሠማይ ፡ የሆነውን ፡ አደራ ፡ ችላ ፡ አትበል
ከሚያገሰግኑ ፡ አፍ ፡ እንዳትፈተን ፡ ልብህን ፡ አትጣ
በተቃዋሚዎችም ፡ ተደናግጠህ ፡ ፈቀቅ ፡ እንዳትል
የጠራህን ፡ ጌታ ፡ እያየህ ፡ ሩጫውን ፡ ቀጥል
ዓለምን ፡ አትርፎ ፡ ነፍሱን ፡ ባያጐድል
ከአገለገለ ፡ በኋላ ፡ ራሱ ፡ እንዳይጣል
ሥጋውን ፡ እየጐሰመ ፡ ለጌታ ፡ ያስገዛል
እንጂ ፡ ራሱን ፡ መቼ ፡ ይሰብካል
አስተዋይ ፡ የማልጠቅም ፡ ባሪያ ፡ ንኝ ፡ ይላል
ክብርን ፡ ሁሌ ፡ ለጌታ ፡ ያስረክባል
አዝ፦ እንደ ፡ ተሰጠህ ፡ አገልግል
ከሠማይ ፡ የሆነውን ፡ አደራ ፡ ችላ ፡ አትበል
ከሚያገሰግኑ ፡ አፍ ፡ እንዳትፈተን ፡ ልብህን ፡ አትጣ
በተቃዋሚዎችም ፡ ተደናግጠህ ፡ ፈቀቅ ፡ እንዳትል
የጠራህን ፡ ጌታ ፡ እያየህ ፡ ሩጫውን ፡ ቀጥል
የልብሳቸውን ፡ ዘርፍ ፡ አስረዝመው ፡ አሸ. (1) . ፡ ሲያሰፉ
ጾመኛ ፡ መስለው ፡ ሊታዩ ፡ ለሰዎች ፡ ፊታቸውን ፡ ሲያጠፉ
አሥራት ፡ መጿት ፡ ሲያወጡ ፡ መለከት ፡ ሲያስነፉ
ግብዞች ፡ ልብን ፡ በሚያይ ፡ ጌታ ፡ . (2) .
የመንግሥቱ ፡ ሠማያት ፡ ደቀመዝሙር ፡ በእውንት ፡ ራሱን ፡ ይመርምር
አዝ፦ እንደ ፡ ተሰጠህ ፡ አገልግል
ከሠማይ ፡ የሆነውን ፡ አደራ ፡ ችላ ፡ አትበል
ከሚያገሰግኑ ፡ አፍ ፡ እንዳትፈተን ፡ ልብህን ፡ አትጣ
በተቃዋሚዎችም ፡ ተደናግጠህ ፡ ፈቀቅ ፡ እንዳትል
የጠራህን ፡ ጌታ ፡ እያየህ ፡ ሩጫውን ፡ ቀጥል
|