እግዚአብሔር ፡ ብቻውን (Egziabhier Bechawen) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 2.jpeg


(2)

አመልከዋለሁ
(Amelkewalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ
በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ
የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ
ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ
ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ

አማሌቅ ፡ በመንገድ ፡ ተቃወመን
ደክመን ፡ ሳለን ፡ መንገድ ፡ ዘጋጋብን
ተዋጊውእግዚአብሄር ፡ ድል ፡ አድርጎልን
ስንት ፡ ጭንቅ ፡ መንገዶችን ፡ አለፍን
ተዋጊው ፡ ወዳጄ ፡ ፊት ፡ ቀድሞልን
ስንት ፡ ጭንቅ ፡ መንገዶችን ፡ አለፍን

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ
በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ
የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ
ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ
ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ

እርምጃችንን ፡ ሊያሰናክሉ ፡ የመከሩ
የክፋት ፡ ሰራዊት ፡ መጥመድን ፡ ሰወሩ
በመንገዳችን ፡ ላይ ፡ እንቅፋት ፡ አኖሩ
ጌታ ፡ ደርሶልን ፡ ፈረሰ ፡ ምክሩ (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ
በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ
የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ
ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ
ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ

ከአውሬ ፡ ጋር ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ታግለናል
ስለነፍሳችን ፡ እንኳን ፡ ተስፋ ፡ ቆርጠናል
በብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ መሀል ፡ ክንዱን ፡ አይተናል
በአምላካችን ፡ ብርታት ፡ ቅጥሩን ፡ ዘለናል (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ
በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ
የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ
ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ
ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ

የጨካኞች ፡ ቁጣ ፡ እስትንፋስ
ቅጥርን ፡ እንደሚመታ ፡ አውሎንፋስ
ባየለበት ፡ ዘመን ፡ በእርሱ ፡ ድል ፡ አድርገናል
በክንዱ ፡ ፅናት ፡ ከሁሉ ፡ ተርፈናል (፪x)

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ
በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ
የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ
ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ
የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ
ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ