አመልከዋለሁ (Amelkewalehu) - ወርቅነህ ፡ አላሮ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ወርቅነህ ፡ አላሮ
(Workneh Alaro)

Workneh Alaro 2.jpeg


(2)

አመልከዋለሁ
(Amelkewalehu)

ዓ.ም. (Year): (2012)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የወርቅነህ ፡ አላሮ ፡ አልበሞች
(Albums by Workneh Alaro)

አዝ፦ አመልክሃለሁ ፡ ብቻውን ፡ አምላክ ፡ ነው (፪x)
አመልከዋለሁ ፡ የማይጠፋው ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ የወደደኝ ፡ በደሙ ፡ ያጠበኝ ፡ አንድዬ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ በማንም ፡ የማለውጠው ፡ ውድ ፡ ወዳጄ ፡ ነው

አመልክሃለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠ ፡ ሌላ ፡ ማነው
አመልከዋለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ሌላ ፡ ማነው

ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ማነው
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ማነው ፡ ማነው

የሚታዩትና ፡ የማይታዩትም ፡ ዙፋናትህ (፪x)
ጌትነት ፡ ወይም ፡ አለቅነት ፡ ሥልጣናት
በሠማይና ፡ በምድር ፡ ያሉት ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ (፪x)
በእርሱ ፡ ተፈጥረዋል ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ፍጡር ፡ አይደለም
በኢየሱስ ፡ ተፈጥረዋል ፡ ወዳጄ ፡ ፍጡር ፡ አይደለም
 
ዲያቢሎስ ፡ የተቀላቀለ ፡ ነገር ፡ ቢሰብክም
ክርስትና ፡ መገለጥ ፡ ነው ፡ አልታለልም
የእግዚአብሔርን ፡ የክብሩን ፡ እውቀት ፡ ብርሃን
በውስጤ ፡ ጨለማን ፡ ያበራ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

በእግዚአብሔርና ፡ በሰውም ፡ መካከል ፡ ያለው ፡ መካከለኛው (፪x)
አንድ ፡ ነው ፡ እርሱም ፡ ሰው ፡ የሆነው ፡ ክርስቶስ ፡ ነው
ነፍሱንም ፡ ለሁሉ ፡ ቤዛ ፡ የሰጠው ፡ የሰጠ
መልክተኛ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ መዳን/ሕይወት ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x)

ብቻም ፡ ብዙ ፡ አማልክትና ፡ ብዙ ፡ ጌቶች ፡ አሉ
ጌታዬ ፡ አይደሉም ፡ በውሸት ፡ ዕውቀት ፡ ሰውን ፡ ያታለሉ
ሠማይም ፡ ቢሆን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ከአማልክት ፡ አሉ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አዳኝ ፡ የተቀባ ፡ አዳኝ ፡ እውነቱ ፡ ሲታይ

አዝ፦ አመልክሃለሁ ፡ ብቻውን ፡ አምላክ ፡ ነው (፪x)
አመልከዋለሁ ፡ የማይጠፋው ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ የወደደኝ ፡ በደሙ ፡ ያጠበኝ ፡ አንድዬ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ በማንም ፡ የማለውጠው ፡ ውድ ፡ ወዳጄ ፡ ነው

አመልክሃለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠ ፡ ሌላ ፡ ማነው
አመልከዋለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው
አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ሌላ ፡ ማነው

ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ማነው
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ማነው ፡ ማነው