የማይተመን ፡ ነው ፡ በዋጋ (Yemaytemen New Bewaga) - ፅዮን ፡ አየለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፅዮን ፡ አየለ
(Tsion Ayele)


(1)

ምራኝ
(Meragn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፅዮን ፡ አየለ ፡ አልበሞች
(Albums by Tsion Ayele)

የዘላለም ፡ አምላክ ፡ መኖሪያዬ
የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ አለኝታዬ
በከበረው ፡ ደምህ ፡ የቀደስከኝ
የመንግሥትህ ፡ ወራሽ ፡ ያረከኝ

የኃጢአት ፡ እዳዬን ፡ ከፍለህ
መተላለፌንም ፡ ደምስሰህ
ማለፍ ፡ ሆኖልኛል ፡ በደምህ
ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይሁንልህ

አዝ፦ የማይተመን ፡ ነው ፡ በዋጋ
ያገኘሁት ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጋ
እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር
አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር (፪x)

መሸ ፡ ነጋ ፡ ሳልል ፡ ዘወትር
ቅኔን ፡ እቀኛለሁ ፡ ለአንተ ፡ ክብር
ማልጄ ፡ ስነሳ ፡ ምሕረትህ
በሌት ፡ አዜማለሁ ፡ እውነትህን

ስለ ፡ እኔ ፡ የዋልከው ፡ ውለታ
ያረክልኝ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ
ተጽፎ ፡ ይኖራል ፡ በልቤ
ሊጠፋ ፡ አይችልም ፡ ከሃሳቤ

አዝ፦ የማይተመን ፡ ነው ፡ በዋጋ
ያገኘሁት ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጋ
እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር
አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር (፪x)

ረክቻለሁ ፡ አርፌያለሁ
ረክቻለሁ ፡ ወደኸኛልና
ረክቻለሁ ፡ አርፌያለሁ
ረክቻለሁ ፡ በልጠህብኛልና

አዝ፦ የማይተመን ፡ ነው ፡ በዋጋ
ያገኘሁት ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጋ
እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር
አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር
እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር
አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር (፪x)