ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (Yeh Lebien Tew Belew) - ፅዮን ፡ አየለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ፅዮን ፡ አየለ
(Tsion Ayele)

Tsion Ayele 1.jpg


(1)

ምራኝ
(Meragn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የፅዮን ፡ አየለ ፡ አልበሞች
(Albums by Tsion Ayele)

ኧረ ፡ ለምን ፡ ይሆን ፡ እንደዚህ
የራሴ ፡ እያለኝ ፡ የሰው ፡ የሚያስመኘኝ
ያለኝን ፡ አስቶ ፡ ሌላ ፡ የሚያሳየኝ

አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x)
ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x)
ምከረው (፪x)

ሳለኝ ፡ ብዙ ፡ ምክኒያት ፡ ተመስገን ፡ ምልበት
ምነው ፡ ማጉረሜ ፡ ሰነፍ ፡ ይሆንኩበት
ያለኝ ፡ ይበቃኛል ፡ ብዬ ፡ እያመሰገንኩ
አንተ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንተን ፡ እያከበርኩ
ልኑር ፡ እባክህ ፡ እርዳኝ ፡ የሌላ ፡ ሳልመኝ
ከበቂ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ አንተ ፡ የሰጠኸኝ

ወገኔ ፡ መልካም ፡ ሲሆንለት
ምነው ፡ ልቤን ፡ ከፋው ፡ ደስታው ፡ ቅር ፡ አሰኘኝ
በመከራው ፡ እኑም ፡ ማመስገን ፡ ተሳነኝ

አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x)
ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x)
ምከረው (፪x)

ደስ ፡ ካለው ፡ ጋራ ፡ አብሮ ፡ ደስ ፡ ይበለኝ
ላዘነውም ፡ ደግሞ ፡ መጽናናት ፡ አድርገኝ
በጐ ፡ ህሊና ፡ ስጠኝ ፡ ሃሳቤንም ፡ አቅና
የአንተን ፡ ልብ ፡ አርግልኝ ፡ የእኔን ፡ ለውጥና
ፍቅርን ፡ ተላብሼ ፡ ትህትናን ፡ ደርቤ
ኖሬ ፡ ላስደስትህ ፡ በለኝ ፡ እንደ ፡ ልቤ

ያም ፡ ለእኔም ፡ ለእኔ ፡ ምኞቴ
እኔና ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ሁልጊዜ ፡ ፀሎቴ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለይልኝ ፡ እኔን ፡ ከእኔነቴ

አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x)
ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x)
ምከረው (፪x)

አንዱ ፡ ሰቀናጣ ፡ ኖሮት ፡ ብዙ ፡ ነገር
ሀብቱ ፡ ተትረፍርፎ ፡ ለምርጫ ፡ ሲቸገር
ሌላው ፡ ደግሞ ፡ ከፍቶት ፡ የሚበላው ፡ አጥቶ
ሲያንቀጠቅጠው ፡ ብርዱ ፡ ውስጡ ፡ ገብቶ
ሲፈራረቁበት ፡ ዝናብና ፡ ፀሐይ
እያለኝ ፡ ካለፍኩበት ፡ እኔም ፡ ዓይኔ ፡ ሲያይ

አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x)
ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x)
ምከረው (፪x)

ልቤን ፡ ፈውሰው
ልቤን ፡ እጠበው
ልቤን ፡ ቀይረው
ልቤን ፡ ልብ ፡ አርገው (፪x)