From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ስለ ፡ ሁኔታዎች ፡ ሳዝን ፡ ሲከፋኝ
የመስቀል ፡ ፍቅርህ ፡ ወዳጄ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ
ሚደርስብኝ ፡ መከራ ፡ እንደ ፡ ብዙ ፡ ደስታ ፡ ቆጠርኩኝ
ውለታህ ፡ መዘነብኝ (፭x)
ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ ጭልም ፡ ሲልብኝ
ወዲያው ፡ መልሶ ፡ ፍቅርህ ፡ ትውስ ፡ ሲለኝ
ነገሩን ፡ ትውት ፡ አድርጌው ፡ ጸልያለሁ/ዘምራለሁ
የታላቅነትህን ፡ ሚስጥር ፡ አስተውላለሁ
የታላቅነትህን ፡ ሚስጥር ፡ አስተውላለሁ (፪x)
ጌታን ፡ ለማስከበር ፡ ከፍሎ ፡ የለ ፡ ዋጋ
አንዱ ፡ በመጋዝ ፡ ሲሰነጠቅ ፡ ሌላው ፡ በጦር ፡ ሲወጋ
አንበሳ ፡ ሲበላ ፡ ሲጠበስ ፡ በዘይት
በድንጋይ ፡ ሲወገር ፡ ሲቃጠል ፡ በእሳት (፪x)
አያሳስበኝም ፡ መከራ ፡ ችግሩ
አያስጨንቀኝም ፡ ውርጭና ፡ ሀሩሩ
የጌታዬ ፡ ሥም ፡ ግን ፡ በዚም ፡ በዚያም ፡ መክበሩ
እሱ ፡ ነው ፡ ቁም ፡ ነገሩ (፬x)
አያሳስበኝም ፡ መከራ ፡ ችግሩ
አያስጨንቀኝም ፡ ውርጭና ፡ ሀሩሩ
የጌታዬ ፡ ሥም ፡ ግን ፡ በዚም ፡ በዚያም ፡ መክበሩ
እሱ ፡ ነው ፡ ቁም ፡ ነገሩ (፲፬x)
|