From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
ትዕግሥት ፡ ዓለሙ (Tigist Alemu)
|
|
፩ (1)
|
ማራናታ (Maranatha)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
|
ቁጥር (Track):
|
፬ (4)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:08
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የትዕግሥት ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች (Albums by Tigist Alemu)
|
|
ባከብርህ ፡ ባመልክህ ፡ ባመሰግንህ
ተባረክ ፡ ተወደስ ፡ ክበር ፡ እያልኩህ
መቼ ፡ ይበቃኛል ፡ አንተን ፡ ሊገልጽህ
ለእኔ ፡ ታደረከው ፡ ጌታ ፡ እየበዛብኝ
በተከፋሁ ፡ ጊዜ ፡ ልቤ ፡ ሃዘን ፡ ሲውጠኝ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ ፈጥነህ ፡ ደረስክልኝ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሆነህ ፡ ነፍሴን ፡ እያጽናናህ
ያንን ፡ ጨለማዬን ፡ በብርሃንህ ፡ አበራህ
ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ወዳጄና ፡ አባቴ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ይህን ፡ ፍቅር ፡ ትቼ (፪x)
በፊትህ ፡ ስበድል ፡ በአመጼ ፡ ስትቀጣኝ
በበደሌ ፡ አዝኜ ፡ ፊትህን ፡ ላይ ፡ ስመኝ
አይተህ ፡ አዘንክልኝ ፡ በንስሃ ፡ ሞልተህ
ጽድቅን ፡ አወጣሃት ፡ ጠላቴን ፡ ረግጠህ
ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ
እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ
ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x)
ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x)
የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ
ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ
እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ
ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x)
ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x)
የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ
የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ
|