ፍሬ ፡ እንዳታጣብኝ (Ferie Endatatabegn) - ትዕግሥት ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ትዕግሥት ፡ ዓለሙ
(Tigist Alemu)

Lyrics.jpg


(1)

ማራናታ
(Maranatha)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የትዕግሥት ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Tigist Alemu)

ልጄ ፡ ሆይ ፡ ህጌን ፡ አትርሳ ፡ ልብህም ፡ ት እዛዛቴን ፡ ይጠብቅ
ብዙ ፡ ዘመናትና ፡ ረጅም ፡ ዕድሜ

ቃልህን ፡ ሰምቻለሁ ፡ ድምፅህን ፡ ሰምቻለሁ
ምክርህን ፡ ሰምቻለሁ ፡ ሰምቻለሁ
ፍሬ ፡ እንዳታጣብኝ ፡ ግን ፡ እፈራለሁ

የሚወድህ ፡ ቃልህን ፡ ይጠብቃል
ትእዛዛትህን ፡ በመንገዱ ፡ ያረጋል
ድምፅህን ፡ ሰምቼ ፡ ጌታ ፡ ካልታዘዝኩኝ
የታለ ፡ ፍቅሬ ፡ ለአንተ ፡ ያለኝ

ምክርህ ፡ ካልተቀየርኩኝ
ከክፉ ፡ ሃሳቤም ፡ ካልተመለስኩኝ
መልኬን ፡ ብቻ ፡ አይቶ ፡ መሄድ ፡ ይሆንብኛል
ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል

ቁጣህም ፡ ሳይብስ ፡ ቅጣት ፡ ሳይመጣ ፡
ጌታ ፡ መልሰኝ ፡ ጨርሼ ፡ እንዳልወጣ
ያኔ ፡ በረከት ፡ ፍሬ ፡ ይበዛልኛል
በመታዘዜ ፡ መውደዴ ፡ ይታያል

የልቤ ፡ መሻት ፡ የውስጥ ፡ ጥማቴ
አክብሬህ ፡ መኖር ፡ እኔስ ፡ በሕይወቴ ፡
ፀጋህን ፡ እሻለሁ ፡ በዚም ፡ ደግሜ