From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ጊዜው ፡ ትዝ ፡ ይለናል ፡ የተጠራንበት
ትዳሩን ፡ ሊያሸንፍ ፡ ሁሉም ፡ በያለበት
ሲወጣና ፡ ሲወርድ ፡ አግኝተህ ፡ ስትጠራው
አልማረክ ፡ ብሎ ፡ "እምቢ" ፡ ያለ ፡ ማነው
አዝ፦ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው
የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው
ሥምህ ፡ አይጠገብ ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው
ደንቆሮዎች ፡ የነበርን ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ሰማን
ከብርና ፡ ከወርቅ ፡ መብለጥህን ፡ ተረዳን
ሙታን ፡ ስታስነሳ ፡ እውር ፡ ስታበራ
ዓይናችን ፡ አይቶሃል ፡ ድንቅ ፡ ሥራ ፡ ስትሰራ
አዝ፦ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው
የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው
ሥምህ ፡ አይጠገብ ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስንጓዝ ፡ በዓለም ፡ ማዕበል ፡ ውስጥ
ነፋሱን ፡ ገሰጽከው ፡ እኛ ፡ እንዳንሰምጥ
ድምፅህ ፡ አይዘነጋም ፡ ያ ፡ የሚያጽናናው
ፍቅርህ ፡ እንደ ፡ ጠል ፡ ነው ፡ ለጠወለገ ፡ ሰው
አዝ፦ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው
የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው
ሥምህ ፡ አይጠገብ ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው
|