Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Tenes

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ=ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ተነሥ አልበም የናዝሬቱ ኢየሱስ

አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ (፪x)

ሕዝብህ በምድረ ግብፅ ኑሮ ቢመራቸው ከበግ ጥበቃ ላይ ሙሴን የጠራኸው የዘመናት ንጉሥ እግዚአብሔር ሆይ ዘንዶውን የወጋህ አንተ አይደለህም ወይ

አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ

የሳተም ይመለስ የዛለም ይበርታ የኃጢአት ምርኮኛ ከእስራት ይፈታ ክንድህን ስንጠብቅ በናፍቆት ዝለናል እስኪ አንድ ጊዜ ጐብኘን ተጠምተናል

አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ

ያለፉት ባሮችህ አስከብረውሃል ኃይልህ ከላይ ሲወርድ ከአንበሳ ገጥመዋል አንካሶች ሮጠዋል ጋኔሎች ወጥተዋል ጊዜ እይለውጥህም እኛም አይተንሃል

አዝ ተነሥ (፬x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ