From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ለምን ፡ ወደድከኝ ፡ አልልህም ፡ በእርግጥ ፡ ወደኸኛል
የፍቅርህ ፡ መግለጫ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ተወግተሃል
አንተ ፡ ለእኔ ፡ የሆንከውን ፡ ያህል ፡ እኔ ፡ ለአንተ ፡ አልሆንኩም
ምን ፡ ያህል ፡ እንደሆነ ፡ አላውቅም ፡ ለክቼ ፡ አላየሁም
አዝ፦ ግን ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ
ስለወደድከኝ ፡ ወድሃለሁ (፪x)
ከእርግማን ፡ ስለ ፡ ዋጀኸኝ ፡ ሞተህ ፡ ሸክሜን ፡ ስለ ፡ ወሰድክ
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ስለ ፡ ሞላኸኝ ፡ ነፍሴን ፡ ስለ ፡ ባረክ
ፀጋህን ፡ አብዝተህ ፡ ስለ ፡ ሰጠኸኝ ፡ ከቶም ፡ ስላልተውከኝ
ምን ፡ ያህል ፡ እንደሆነ ፡ አላውቅም ፡ ለክቼ ፡ አላየሁም
አዝ፦ ግን ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ
ስለወደድከኝ ፡ ወድሃለሁ (፪x)
ደስ ፡ ላሰኝህ ፡ እቀናለሁ ፡ በሕይወቴ ፡ ላከብርህ
ሆኖም ፡ ከቶ ፡ አልጠቀምኩህም ፡ ሁሌ ፡ ሳሳዝንህ
ይልቅ ፡ ብዙ ፡ አድክሜሃለሁ ፡ የትም ፡ እየቀረሁ
ብዙም ፡ ስላላፈራሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍቶኝ ፡ አለቅሳለሁ
አዝ፦ ግን ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ
ስለወደድከኝ ፡ ወድሃለሁ (፪x)
|