Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Nefsie Wede Amlakua

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ነፍሴ ወደ አምላኳ አልበም የናዝሬቱ ኢየሱስ

አዝ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ

ሲተጉ የሚያገኛቸው ሲመጣ ጌታቸው በመክሊታቸው የሰሩ ምሥጋና አላቸው አገልግሎቱን ያልናቀ በጥቂቱ ታምኖ ብድራቱን ይቀበላል ሥራው ተፈትኖ

አዝ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ

አደራው ከቶ የማይገዳቸው ቸልተኞች የጌታቸውን መመለስ የረሱ ዝንጉዎች ዕድላቸው ለቅሶ ነውና ዋይታ እንዳይጠብቀኝ መንፈስህ ዘወትር ያንቃኝ ለክብርህ አቁመኝ

አዝ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ

ጥቂት ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት እንደ ሆነ መች አጣሁት ከቶ የእኔ ሕይወት እንግዲያው ታከተኝ ሳልል ልሩጥ ለጌታዬ የሰነፍ ሰው ሞት እንዳልሞት ልፅና በዓላማዬ

አዝ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ሌት ተቀን ልስራና ስራዬን ልጨርስ

መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ አበቃሁኝ ኃይማኖትን ጠብቄያለሁ ሩጫውን ጨረስኩኝ እንደ ጳውሎስ ለማለት ተፈፀመ እንደ ኢየሱስ ምሥጋናዬንም እንዳቀርብ ለሠራዊት ንጉሥ

አዝ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ቶሎ ቶሎ ብዬ ስራዬን ልጨርስ ነፍሴ ወደ አምላኳ ሥጋም ወደ አፈሩ ሳይመለስ ሌት ተቀን ልስራና ሥራዬን ልጨርስ