From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ከጥፋት ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ከረግርግ ፡ ጭቃ ፡ ያወጣኝ
እግሬን ፡ በድንጋይ ፡ ላይ ፡ አቁሞ ፡ ያፀናኝ
በፀጋው ፡ ደግፎ ፡ በሕይወት ፡ ያኖረኝ
ከክፉ ፡ ፍላጻ ፡ በእጁ ፡ የከለለኝ
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ስገጂለት
መሀሪው ፡ ጌታዬ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
በሕይወቴ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ልገዛለት
ቸርነቱን ፡ ልንገር ፡ ምህረቱን ፡ ልዘምር
ቅኔን ፡ ልቀኝለት ፡ ኦ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት
ድካምን ፡ ህመምን ፡ ቁስልን ፡ ስብራትን ፡ አይቶ
ዘመድ ፡ ርቆ ፡ ሲቆም ፡ ኢየሱስ ፡ ተጠግቶ
በፍቅር ፡ አክሞ ፡ ሕይወትን ፡ ያድሳል
ለውለታው ፡ ምላሽ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ይገኛል
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ስገጂለት
መሀሪው ፡ ጌታዬ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
በሕይወቴ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ልገዛለት
ቸርነቱን ፡ ልንገር ፡ ምህረቱን ፡ ልዘምር
ቅኔን ፡ ልቀኝለት ፡ ኦ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት
የጫንቃዬን ፡ ሸክም ፡ ጌታዬ ፡ ደርሶ ፡ ጣለልኝ
የዕዳዬን ፡ ጽሕፈት ፡ በሞቱ ፡ ሻረልኝ
ምህረቱ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያሳየው
ከእግሩ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ፡ ጌታዬን ፡ ላክብረው
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ስገጂለት
መሀሪው ፡ ጌታዬ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
በሕይወቴ ፡ ሁሉ ፡ እኔም ፡ ልገዛለት
ቸርነቱን ፡ ልንገር ፡ ምህረቱን ፡ ልዘምር
ቅኔን ፡ ልቀኝለት ፡ ኦ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝለት
|