Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Kamlakachew Beqer

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ከአምላካቸው በቀር

አዝ ከአምላካቸው በቀር ማንንም እንዳያመልኩ ለወርቁ ምስል እንዳይሰግዱ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ወዳጆቹን ያዳነ በእርሱ የታመኑትን የሲድራቅ የሚሳቅ የአብድናጐም አምላክ ለዘለዓለም ይባረክ

እንደ እርሱ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና ከእቶኑ እሳት ሊያድናቸው ችሏልና ማዳን የእርሱ ነውና (፪x)

አዝ ከአምላካቸው በቀር ማንንም እንዳያመልኩ ለወርቁ ምስል እንዳይሰግዱ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ወዳጆቹን ያዳነ በእርሱ የታመኑትን የሲድራቅ የሚሳቅ የአብድናጐም አምላክ ለዘለዓለም ይባረክ

ጌታ ተናገረ እኔም ይህንን ብቻ ሰማሁ ኃይል የእግዚአብሔር መሆኑን ተገነዘብሁ እሳቱ ሲያጠፋ አየሁ (፪x)

አዝ ከአምላካቸው በቀር ማንንም እንዳያመልኩ ለወርቁ ምስል እንዳይሰግዱ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ወዳጆቹን ያዳነ በእርሱ የታመኑትን የሲድራቅ የሚሳቅ የአብድናጐም አምላክ ለዘለዓለም ይባረክ

ሰውነታችሁን ብትሰጡ ሳትሰስቱ እግዚአብሔር ይሰራል አይፋጅም ከቶ እሳቱ ሥሙን አስከብሩ በርቱ (፪x)

አዝ ከአምላካቸው በቀር ማንንም እንዳያመልኩ ለወርቁ ምስል እንዳይሰግዱ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ወዳጆቹን ያዳነ በእርሱ የታመኑትን የሲድራቅ የሚሳቅ የአብድናጐም አምላክ ለዘለዓለም ይባረክ (፫)