Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Bewnet Asadegen

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ በእውነት አሳድገ አልበም የናዝሬቱ ኢየሱስ

አዝ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር

በክርስትናችን ዕድሜ ቆጥረን በልምምዳችን ኮርተን በትህትና መማሩ ቀረና እድገታችን ቆመ ታበይንና

አዝ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር

ባስተያየታችን ጠቢባን ነን ትንኝን እናጠራለን ራሳችንን ማንጻት ሳይቻለን የሌላውን ጉድፍ እናያለን

አዝ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር

ማደጋችንን እዩልን እያልን በከንቱም እየታበይን አንተንም በዚህ እያሳዘንን ሳይታወቀን ስንቶችን ጐዳን

አዝ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር

እንደ ሕጻናት የዋሆች አርገን ንጹህ ልብን መልስልን ዓይናችንን እየገለጥህ አንተው አመላልሰን በብርሃንህ

አዝ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር

በቃል በስርአት ሙታን ሆነን በፍቅር እየታነፅን በእውነት እንደግ ወደ ኢየሱስ እየታበይን እንደምን እንነስ