From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው
ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው
ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው
የማይጠፋውን ፡ ምረጠው
ጌታ ፡ ይሻልሃል
ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነህ (፪x)
ለማያጠግብህ ፡ እሮጠህ
ምናምንቴ ፡ ነገር ፡ ወደህ
ረብ ፡ ረድኤት ፡ በማይሆነው
በኩረነትህን ፡ ሸጥከው
አዝ፦ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው
ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው
ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው
የማይጠፋውን ፡ ምረጠው
ጌታ ፡ ይሻልሃል
ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነህ (፪x)
ብዙዎች ፡ ወደቁ ፡ ተጠልፈው
በገንዘብ ፡ ፍቅር ፡ ተነድፈው
ብልጽግና ፡ ያታልላል
ይሁዳ ፡ ጌታውን ፡ ሽጧል
አዝ፦ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው
ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው
ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው
የማይጠፋውን ፡ ምረጠው
ጌታ ፡ ይሻልሃል
ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነህ (፪x)
ሰይፍ ከዋጠው፡ የበለጠ
የኃጢአት ፡ ዱር ፡ ብዙ ፡ ዋጠ
አንተን ፡ የዋጠህ ፡ ምንድን ፡ ነው
ነፍስህን ፡ አንቆ ፡ የያዘው
አዝ፦ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው
ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው
ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው
የማይጠፋውን ፡ ምረጠው
ጌታ ፡ ይሻልሃል
ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነህ (፪x)
|