Tesfaye Gabisso/Egziabhier Menfes New/Lamesgeneh Zariem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ላመስግንህ ዛሬም አልበም እግዚአብሔር መንፈስ ነው

ትንፋሼንና መንገዴ ሁሉ በእጅህ ይዘህ እንደ ዓይንህ ብሌን አርገህ ለእኔ ተጠንቅቀህ ከሚጐዳኝ ነገር ዘወትር ጋረድክ ሰውረህ ተመሥገን ከማለት ሌላ ለአንተ ምን ልክፈልህ

አዝ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘላለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ

በሀዘን ስመታ ሲከፋኝም አንዳንድ ጊዜ ከብዶ ሲጫጫነኝ ሲደራረብብኝ ትካዜ የመፅናናት ጌታ ማን እንደ አንተ ደረሰልኝ የልቤን ተካፍሎ አይዞህ ሊለኝ ሊያበረታኝ

አዝ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘላለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ

ራሴን አውቀው አለሁ እጅግ አስቀያሚ ነበርኩ ምስኪን አላማ ቢስ በኃጥያት የተቅበዘበዝኩ ግን እንዲያው ወደኸኝ ሰው ሆኛለሁ በአንተ ብርታት በቂ ቃል የለኝም ልገልፅ የውለታህን ብዛት

አዝ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘላለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ

አህዛብ ባያውቁህም የእኔ ነፍስ ግን ታውቅሃለች የፍቅር ፊትህን በእየለት ትናፍቃለች ያለ አባትነትህ መኖር ከቶ አይሆንላትም መሳይ አጭበርባሪ ሁሉ ከአንተ አይነጥላትም

አዝ ላመስግንህ ዛሬም የእኔ ጌታ ስለማይነገር ስጦታህ ስላማይቆጠር ውለታህ በእውነት አንተ ታማኝ ነህ ዘላለም ይወደስ ይክበር ታላቅ ሥምህ