Tesfaye Gabisso/Christian Teshagere/Zemenu Fetene

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ዘመኑ ፈጠነ አልበም ክርስቲያን ተሻገረ

አዝ ዘመኑ ፈጠነ ሮጠ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን አደራ አስቡ

ሰዓቱ ሊሞላ በቅርብ ነው ያለው መለከት ሊነፋ በቅርብ ነው ያለው ነገሩ ሊያከትም በቅርብ ነው ያለው ጌታም ከተፍ ሊል በቅርብ ነው ያለው

አዝ ዘመኑ ፈጠነ ሮጠ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን አደራ አስቡ

ሰማያት ሲከብዱ ደመናው ሲጠቁር ምድራችን ስታምር ነገር ሲቀያየር ምን አዚም ኖረብን እንዳናይ ጊዜ አጥሮን ተው ነቃ እንበል እናቁም አንቅልፍን

አዝ ዘመኑ ፈጠነ ሮጠ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን አደራ አስቡ

ሰዉ ሲተራመስ ሞትን ለመሳለም ከአምላክ ተለይቶ በኃጢያት ሲታመን ጠቢቡ እንኳን ሲስት በሰይጣን ሲታለል ተነሱ አንናገር ለነፍስ እንታገል

አዝ ዘመኑ ፈጠነ ሮጠ ገሰገሰ የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ የተጣለብንን አደራ አስቡ

ለራሱ ያልሞተ እራሱን ያልከዳ ጌታ የማይገዛው ለኃጥያት ያልታገለ በምኑ ይመስክር ልቡ ይንቀጠቀጣል ዋጋም ክፈል ሲባል ትቶ ይፈረጥጣል