Tesfaye Gabisso/Christian Teshagere/Yeseralegnen Denq

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ
ርዕስ የሰራልኝን ድንቅ
አልበም ክርስቲያን ተሻገረ

አዝ
የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ
ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ
በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ (፪)

በእለት እርምጃዬ እግሬን የሱስ ቀድሞ
ምህረቱን አብዝቶ ተዓምራቱን ደግሞ
አሳየኝ አምላኬ የከበረ ነገር
እንደዚህ ሊመራኝ ወደ ፃድቃን አገር (፪x)

አዝ
የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ
ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ
በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ (፪)

በቀኝ በግራዬ አድፍጦ አድብቶ
መልካም መሰል አጥፊ ወጥመዱን ዘርግቶ
ጌታ ግን ሲያድነኝ በጦር ተደራጅቶ
ዲያብሎስ ሊያጠቃኝ
ነበር ተሰናድቶ (፪x)

አዝ
የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ
ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ
በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ (፪)

እርሱ ቅጥር ሲቀጥር በእምላኬ እየዘለልኩ
ወጥመድ ሲዘረጋ እኔም እያመለጥኩ
በእኔ ብርታት ሳይሆን በጌታ እየታመንኩ
ሩጫ ቀጥላለሁ ሁሉን እያሸነፍኩ (፪x)
አዝ
የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ
ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ
በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ (፪)

በዘለዓለም መድህን ከጥልቁ ወጥቼ
ከአባት ከእናት ዘመድ የሚበልጥ አግኝቼ
በአህዛብ መሃከል ለርሱ ዘምራለሁ
የከበረ ሥሙን አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ

የሰራልኝን ድንቅ ታሪኩን ላውጋችሁ
ሰዎች እስኪ ስሙ ትምህርት ይሁናችሁ
በጌታ ይታመን ይጽናና ልባችሁ (፪×)