Tesfaye Gabisso/Awon Yehonal/Yehayalan Hulu Hayal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ሰማይን የሰራ የምድርም ፈጣሪ በዘለዓለም ዙፋን ለዘለዓለም ኗሪ ገናናነትህን ሰማያት ያውቃሉ ምድርና ሞላዋም ይመሰክራሉ።

የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ።

በነገስህ ጊዜ ክብርህን ስትለብስ ለተጠቃው ህዝብህ ፊትህን ስትመልስ ድንቅ አድራጐትህን በምድር ስታደርግ በጽድቅህ ስትፈርድ አመጻን ስትጠርግ።

የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ።

ቃልህን ስትሰጥ በሲና ተራራ በልጆችህ ሰፈር በበረሃው ስፍራ በክብር እሳትህ ተራራውን አጤስከው በመረጥካቸው ፊት ክብርህን ገለጽከው

የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ።

የተዳፈሩህን የተነሱብህን ልክህን ሳያውቁ የታጠቁብህን እየቀጣሃቸው ተረቶች ሆነዋል ተፈርተህ ተከብረህ አንተ ግን ኖረሃል።

የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ። x2