Tesfaye Gabisso/Awon Yehonal/Serah Yamesegenehal

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ሥራህ ያመሰግንሃል

ሥራህ ያመሰግንሃል ቅዱሳን ያከብሩሃል ጌትነትህም ገብቷቸው ተንበርክኳል ጉልበታቸው

አዝ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ተመስገን

እውነትህን ጠብቀሃል ለተበደሉት ፈርደሃል የተጠቃውን ታድገሃል በማዳንህ ከፍ ብለሃል

አዝ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ተመስገን

ደሃ አደጉን ተቀብለህ ለተራበ ምግብን ሰጥተህ ምጻተኛ አስጠግተሃል ግዞተኛውን ፈተሃል

አዝ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ተመስገን

የተቀደሰ ሥምህን በዜማ ቅኔ ላመስግን በአንተ ሆኖልኝ የመዳን ቀን ስለወጣሁ ከሰቀቀን

አዝ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (፫x) ኢየሱስ ተመስገን