Tesfaye Gabisso/Abietu Mebareken Barken/Abietu Mebareken Barken
ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ አቤቱ መባረክን ባርከን አልበም አቤቱ መባረክን ባርከን
አዝ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ
ያቤጽንም ሰምተሃል እንደዚህ ሲለምንህ ነፍሱን ባርከህለታል አገሩንም አስፍተህ
አዝ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ
በልጅህ ስቃይና በጣር የተወለድን እኛም ፍሬዎችህ ነን አስባስበህ ጠብቀን
አዝ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህየእኛ ተስፋ
ከፊትህ አትጣለን እንማጸንሃለን በሞገስህ አስበን በምህረትህ ጐብኘን
አዝ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ
ሰማያቱም ይከፈቱ መንፈስህ ይፍሰስልን ሕይወታችን ትረስርስ ነፍሳችን ትጥገብልን
አዝ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ
ብቻችንን አንቅር አብዛን እየባረክህ አበልጽገን በፀጋህ ታደገን በቃልህ
አዝ አቤቱ መባረክን ባርከን አገራችንን አስፋ እጅህም በእኛ ላይ ትሁን አንተ ነህ የእኛ ተስፋ
እግዚአብሔርን በማወቅ ምድር እስክትሞላ ምልጃችን ይቀጥላል ጉልበታችን ሳይላላ