ተነስ (Tenes) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Tesfaye Chala 5.jpeg


(5)

ይታይ
(Yetay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

 
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ነው (ሆ)
ስሙ ፡ ሲጠራ ፡ ይሰራል ፡ አየነው ፡ ይኸው (ሆ)
በጌትነቱ ፡ ችሎት ፡ አምኖ ፡ ሚስማማ
እርሱ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚል ፡ ድምጹን ፡ ያሰማ (፪x)

አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ
ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ
ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ
ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ

ይሰማ ፡ አዳዲስ ፡ ዜማ ፡ በድል ፡ ቀን ፡ የግል ፡ ዝማሬ
እንደተባለው ፡ አልሆነም ፡ ውሸት ፡ ነው ፡ የጠላት ፡ ወሬ
የእኛ ፡ አምላክ ፡ ስሙ ፡ ሲጠራ ፡ ከሰማይ ፡ በእሳት ፡ መልሷል
ይህንን ፡ የሰማ ፡ ያያ ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ችሎ ፡ ይቀመጣል

አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ
ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ
ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ
ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ

ተነስ!

በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ የሚኖር ፡ ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል
ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ያድራል
እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ
አምላኬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ
እርሱ ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከሚያስደነግጠው ፡ ነገር ፡ ያድናል
በላባዎቹ ፡ በላባዎቹ ፡ ይጋርደኛል
በክንፎቹ ፡ በታች ፡ ትተማመናለች ፡
እውነት (፫x) ፡ እውነት ፡ እንደጋሻ (፪x) ፡ ይከብበኛል???

በሌሊት ፡ ግርማ ፡ በቀን ፡ ከሚበር ፡ ፍላጻ
በጨለማ ፡ ከሚሄድ ፡ ክፉ ፡ ነገር
ከአደጋና ፡ ከቀትር ፡ ጋኔን ፡ አትፈራም
በአተገብህ ፡ ሺ ፡ በቀኝህ ፡ አስር ፡ ሺ ፡ ይወድቃሉ
ወደአንተ ፡ ግን ፡ አይቀርቡም
በዐይኖችህ ፡ ብቻ ፡ ትመለከታለህ
የሃጢአንን ፡ ብድራት (፪x) ፡ ታያለህ

አቤቱ ፡ አንተ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ ልዑልን ፡ መጠጊያ ፡ ያደረጉ
ክፉ ፡ ነገር ፡ ወደአንተ ፡ አይቀርብም ፡ መቅሰፍትም ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ አይገባም
በመንገድህ ፡ ይጠብቁህ ፡ ዘንድ ፡ መልአክትን ፡ ስለአንተ ፡ ያዛቸዋል
እግርህን ፡ በድንጋይ ፡ እንዳትሰናከል ፡ በእጆቻቸው ፡ ያነሱሃል
በተኩላና ፡ በእባብ ፡ ላይ ፡ ትጫማለህ ፡ አንበሳውና ፡ ዘንዶውን ፡ ትረግጣለህ
በእኔ ፡ ተማምኗልና ፡ አስጥለዋለሁ ፡ ስሜን ፡ አውቋልና ፡ እጋርደዋለሁ

የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ ነው (ሆ)
ስሙ ፡ ሲጠራ ፡ ይሰራል ፡ አየነው ፡ ይኸው (ሆ)
በጌትነቱ ፡ ችሎት ፡ አምኖ ፡ ሚስማማ
እርሱ ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ የሚል ፡ ድምጹን ፡ ያሰማ (፪x)

አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ
ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ
ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ
ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ

የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ በድኖች ፡ አይሰሙ ፡ ጆሮ ፡ እያላቸው
ይጥሩት (፬x) ፡ ተኝቶ ፡ ይሆን ፡ አምላካቸው
የእኔ ፡ ግን ፡ አምላክ ፡ ግን ፡ የኤልያስ ፡ ስጠራው ፡ ከላይ ፡ የሰማኝ
ተማምኜው ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አምኜው ፡ ሥጋት ፡ አይገባኝ

አዝ፦ ተነስ ፡ በገና ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነስ ፡ ማሲንቆ ፡ ሆይ ፡ ተነስ
ተነስ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነስ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ
ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፤ ተነሽ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ
ተነሽ ፡ እኔም ፡ እነሳለሁ ፤ ተነሽ ፡ አምላኬ ፡ እንዲወደስ (፪x)