From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ተስፋዬ ፡ ጫላ (Tesfaye Chala)
|
|
፮ (6)
|
ይታይ (Yetay)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፫ (2011)
|
ቁጥር (Track):
|
፮ (6)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Chala)
|
|
ያሰቡት ፡ ሳይሰምር ፡ ሲቀር ፡ ሆኖ ፡ እንደህልም
በእኩለ ፡ ቀንም ፡ ላይ ፡ በጊዜ ፡ ሲጨልም (፪x)
በዕድሜ ፡ ያከማቹት ፡ በዋዛ ፡ ሲበተን
በመከራ ፡ እሳት ፡ ማንነት ፡ ሲፈተን (፪x)
ሁኔታውን ፡ ሳይሆን ፡ ቃልህን ፡ አምናለሁ
ታድናለህ ፡ ብዬ ፡ ስንቴ ፡ ዘምሬያለሁ
ወጀቡ ፡ ቢበዛም ፡ በአንተ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም
ይዘንባል ፡ እላለሁ ፡ ደመናውን ፡ ባላይም
አዝ፦ (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀሐይ ፡ ትወጣለች
(ቀን ፡ አለ) ፡ ይኸ ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል
(ቀን ፡ አለ) ፡ የታመንኩት ፡ ጌታ
(ቀን ፡ አለ) ፡ በክብሩ ፡ ይመጣል
(ቀን ፡ አለ) ፡ ፀጋ ፡ ልኮልኛል
(ቀን ፡ አለ) ፡ እሸጋገራለሁ
(ቀን ፡ አለ) ፡ በአስጨነቀኝ ፡ እራስ ፡ ላይ
(ቀን ፡ አለ) ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ (፪x)
የሕይወት ፡ ቀመሩ ፡ መውረድና ፡ መውጣት
ነፍሴ ፡ ምድረበዳው ፡ ውጊያው ፡ ቢያሰለቻት
ዓይኖቼ ፡ ሳይወዱ ፡ ተገደው ፡ ቢያለቅሱ
የድል ፡ መዝሙሮቼ ፡ ለዛሬ ፡ ቢረሱ
እንደማያልፍ ፡ የለም ፡ ይህን ፡ ቀን ፡ አልፋለሁ
ጌታዬ ፡ ሲመጣ ፡ በድል ፡ እወጣለሁ
ይህ ፡ ሰው ፡ አበቃለት ፡ ያለው ፡ ጠላቴ ፡ ነው
በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ ሲወድቅ ፡ አየዋለሁ
አዝ፦ (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀሐይ ፡ ትወጣለች
(ቀን ፡ አለ) ፡ ይሄ ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል
(ቀን ፡ አለ) ፡ የታመንኩት ፡ ጌታ
(ቀን ፡ አለ) ፡ በክብሩ ፡ ይመጣል
(ቀን ፡ አለ) ፡ ፀጋ ፡ ልኮልኛል
(ቀን ፡ አለ) ፡ እሸጋገራለሁ
(ቀን ፡ አለ) ፡ ባስጨነቀኝ ፡ እራስ ፡ ላይ
(ቀን ፡ አለ) ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ
በወይን ፡ ሃረግ ፡ ፍሬ ፡ ቢታጣ ፡ የሚቀመስ
ምንም ፡ እንኳን ፡ ዛሬ ፡ ባታፈራ ፡ በለስ (፪x)
በጐች ፡ ከማደሪያው ፡ ከበረት ፡ ቢታጡ
እርሾችም ፡ ጠውልገው ፡ መብልን ፡ ባይሰጡ (፪x)
እኔ ፡ ግን ፡ በእግዚአብሔር ፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በከፍታዎችም ፡ ላይ ፡ ያራምደኛል
በመድሃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ
ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘወትር ፡ ሃይሌ ፡ ነው
አዝ፦ (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀሐይ ፡ ትወጣለች
(ቀን ፡ አለ) ፡ ይሄ ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል
(ቀን ፡ አለ) ፡ የታመንኩት ፡ ጌታ
(ቀን ፡ አለ) ፡ በክብሩ ፡ ይመጣል
(ቀን ፡ አለ) ፡ ፀጋ ፡ ልኮልኛል
(ቀን ፡ አለ) ፡ እሸጋገራለሁ
(ቀን ፡ አለ) ፡ ባስጨነቀኝ ፡ እራስ ፡ ላይ
(ቀን ፡ አለ) ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ (፪x)
(ቀን ፡ አለ)
|