ቅዱስ (Qedus) - ተስፋዬ ፡ ጫላ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጫላ
(Tesfaye Chala)

Tesfaye Chala 5.jpeg


(5)

ይታይ
(Yetay)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጫላ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Chala)

ክብሩ ፡ ሰማያትን ፡ ምድርን ፡ ሸፍኗል
ለሃያልነቱ ፡ ምን ፡ ቃላት ፡ ይገኛል
(፪x)
መልአክት ፡ በፊቱ ፡ ሳያቋርጡ ፡ ቅዱስ ፡ ይሉታል
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ ይህ ፡ ቅዱስ
በብዙ ፡ ክብር ፡ በብዙ ፡ ፍርሃት ፡ ይሰግዱለታል
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አ ፡ ቅዱስ
በሰማይ ፡ ሆኖ ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ሁሉን ፡ የረታ
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ
የማይለወጥ ፡ የማይቀየር ፡ የክብር ፡ ጌታ
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አ ፡ ቅዱስ ፡ አይ ፡ ቅዱስ ፡ ዘለዓለም
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘለዓለም (፫x)
እንደእግዚአብሔር ፡ የለም

ለታረደው ፡ በግ ፡ ኃይል ፡ ክብር ፡ ባለጠግነት
ሊቀበልህ ፡ ይገባል ፡ አምልኮ ፡ በረከት
(፪x)
ሲሉ ፡ መላእክት ፡ በታላቅ ፡ ዜማ ፡ ከሩቅ ፡ ይሰማል
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ ይህ ፡ ቅዱስ
ፍጥረት ፡ በቋንቋው ፡ አሜን ፡ እያለ ፡ ይተባበራል
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ
ለሕያው ፡ ለሆነው ፡ ለነበረ ፡ ለአለ ፡ ለሚመለሰው
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ
አምልኮ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ይድረሰው
ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ
አይ ፡ ቅዱስ ፡ ዘላለም
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘላለም (፫x)
እንደእግዚአብሔር ፡ የለም
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘላለም (፫x)
እንደእግዚአብሔር ፡ የለም